Monday, April 29, 2013
የተማሪዎች ሪፖርት ካርድ አዘገጃጀት
መምህራን የሪፖርት ካርድ ለተማሪዎች የሚያዘጋጁበት ብዙ ጥሩ ዘዴ አላቸው፡፡ እንደ አማራጭ መላ የሚያገለግል ሌላም ቀላል ኮምፒውተራዊ ዘዴ አለ፡፡ ኮምፒውተር ለአገልግሎታችን መቀላጠፍ የሚረዱ፤ ብዙ መላዎች እንዳሉት ግልጽ ነው፡፡ ከእነዚህ መላዎች ውስጥ የሚከተሉትን ጥያቄዎቻችንን የሚመልስ ትምህርታዊ የሥልጠና ጽሑፍ ተዘጋጅቷል፡፡ የትምህርቱን ጥቅም ለመረዳት፤ የጥያቄዎቹን ክብደት መረዳት ይበጃል፡፡
ጥያቄ
1. ለ200 ተማሪዎች፤ ለእያንዳንዱ፤ በየትምህርት ዘርፉ ያገኙትን ነጥብ ለመጻፍ፤ እና ትክክለኛ ሪፖርት ካርድ ለማዘጋጀት፤ መምህራን ምን መላ ይጠቀማሉ?
2. ትምህርት ቤቱ፤ ለ1000 ምእመናን እና ወላጆች፤ የግል ደብዳቤ መላክ ቢያስፈልግ፤ እንዴት ይሰራዋል፡፡ ስማቸው ያልተሞላ 1000ሺ ደብዳቤ አባዝቶ፤ ከዚያ የ1000 ሰዎችን ስም በየደብዳቤው ይጽፋል? ወይስ…ለሚመለከተው ሁሉ ብሎ የጅምላ ደብዳቤ ያዘጋጃል?
እንዲህ ያሉ ስራዎች፤ ቀላል ቢሆኑም፤ አድካሚ እና ጊዜ ፈጂ የሚሆኑበት ጊዜ አለ፡፡ ብዙ ስህተትም ሊሰራ ይችላል፡፡
እኒህን ጥያቄዎች የሚመልስ የስልጠና ትምህርት ለማግኘት ይህንን ይጫኑ ወይም Resources በሚለው ገጽ ውስጥ ገብታችሁ፤ የሜይል መርጅ ሥልጠና How to Lesson የሚለውን ተጫኑ፡፡
Wednesday, April 24, 2013
Student Report Card Template
Over 150 Regular Student of Debere Meheret Kids Education Department will receive their First Quarter 2013 Report Card.
To see the Report card template click here
To see the Report card template click here
Monday, April 1, 2013
የሩብ ዓመት ፈተና ተሰጠ
መምህራን የትምህርት ዘዴያቸውን ውጤታማነት የሚገመግሙበት፤
ወላጆች ልጆቻቸው መማር አለማማራቸውን የሚያረጋግጡበት አንዱ መንገድ ፈተና መስጠት ነው፡፡ የአዳጊዎች ትምህረት ክፍልም ማርች
31 ቀን 2013፤ በሥሩ ለሚማሩ ከ150 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የአንደኛ ሩብ ዓመት ፈተና ሰጠ፡፡
ፈተናው የአማርኛ ቋንቋ እና የሃይማኖታዊ እውቀትን ለመመዘን የተዘጋጀ ሲሆን፤ የተሰጠውም በሁለት አይነት መንገድ ነው፡፡ 1ኛ በክፍል ውስጥ
ፈተና 2ኛ እቤት በሚወሰድ ፈተና፡፡
የክፍል ውስጥ ፈተናው፤ የቡድን እኛ የግል ጥያቄዎችን ያጠቃለለ ሲሆን፤ እያንዳንዱ
ተማሪ ያለበትን ትክክለኛ የእውቀት ደረጃ ለመመዘን ይረዳል በሚል እሳቤ የተደረገ ነው፡፡ እቤት የሚወሰደው ፈተና ዋና አላማ፤ ወላጆች
ልጆቻቸውን በማስተማር ያላቸውን ተሳትፎ ለመመዘን ሲሆን፤ ጥያቄዎቹ የተዘጋጁትም ተማሪዎቹ የወላጆቻቸውን እርዳታ ካላገኙ በቀር በግል
ለመስራት እንዲቸገሩ ታስቦ ነው፡፡ ልጆቹ እቤት በወሰዱት ፈተና የሚያገኙት ውጤት፤ የወላጆቹ የድጋፍ መጠን መለኪያም የሚሆነው ለዚህ
ነው፡፡
በሚቀጥሉት ሳምንታትም ውስጥ ሁለት ዋና ዋና ተግባራት እንደሚከናወኑ ይጠበቃል፡፡
- የተማሪዎችን ምዘና ውጤት ለወላጆች ማሳወቅ የመጀመርያው ሥራ ሲሆን፤ ለሁሉም ተማሪዎች ወጥ የሆነ ፎርማት ያለው የፈተና ሪፖርት ማድረጊያ ቅጽ እየተዘጋጀ ነው፡፡
- መምህራኑ እና አስተባባሪዎች ፈተናውን በተመለከተ የጋራ ውይይት ያደርጋሉ፡፡ በውይይቱም፤ መምህራኑ የፈተናውን አዘገጃጀት እና አሰጣጥ ሥርዓት በተመለከተ ስኬቶችን እና ድክመቶችን መዝነው፤ ለወደፈቱ የሚጠቅሙ ማሻሻያ እና ማስተካከያ መላዎችን እንዲቀይሱ ይጠበቃል፡፡
Wednesday, March 20, 2013
የሚዲያ ክፍል አገልግሎቱን ሊጀምር ነው
ሚዲያ
ክፍል፤ Print, Video,
Audio, Web, ITን የሚያጠቃልል አገልግሎት ነው፡፡ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ፤ አዳጊ
ልጆች ሃይማኖታቸውን፤ ቋንቋቸውን እና ባህላቸውን በቴክኖሎጂካዊ
መላ እንዲማሩ ማድረግ ሲሆን የአገልግሎቱ ፍሬም የሚለካው ለአዳጊዎች በሚያቀርበው ቴክኖሎጂካዊ አገልግሎት ነው፡፡ በተዛማጅም፤ አስፈላጊ
ሆኖ ሲገኝ፤ የሚዲያ ክፍል ለመምህራን፤ ለተማሪዎች ወላጆች እና ለካህናት የሙያ ድጋፍም ሊሰጥ ይችላል፡፡
1. Laptop
2. DLP Projector
3. Printer (Laser Jet monochrome)
4. Printer (Color)
5. Overhead Projectors
ዋናዎቹ ናቸው፡፡
የሚዲያ ክፍል፤ አገልግሎቱን ለመጀመር በመምህራን እና በወላጆች የሚሞላ አጭር መጠይቅ
ያዘጋጀ ሲሆን፤ የሚመለከታቸው ሁሉ መጠይቁን ሞልተው ለሚዲያ ክፍል ወይም ለአዳጊዎች ክፍል አስተባባሪዎች እንዲሰጡ ይጠበቃል፡፡ መጠይቁን ለማየት ይህንን ይጫኑ
Thursday, March 7, 2013
የመጀመርያ ሩብ ዓመት ፈተና ይሰጣል
News Report posted by Hanna
በዚህ
በያዝነው ወር (ማርች 2013) መጨረሻ ሳምንት ላይ፤ በደብሩ የአዳጊዎች ትምህርት ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች በሙሉ የመጀመርያ ሩብ
ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል፡፡ ፈተናው የሚዘጋጀው በየክፍሉ በሚያስተምሩ መምህራን ሲሆን፤ ፈተናው ከሥርዓተ ትምህርቱ ይዘት ጋርመጣጣሙ ከተረጋገጠ በኋላ፤ ለተማሪዎች ይሰጣል፡፡
በዚህ
በያዝነው ወር (ማርች 2013) መጨረሻ ሳምንት ላይ፤ በደብሩ የአዳጊዎች ትምህርት ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች በሙሉ የመጀመርያ ሩብ
ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል፡፡ ፈተናው የሚዘጋጀው በየክፍሉ በሚያስተምሩ መምህራን ሲሆን፤ ፈተናው ከሥርዓተ ትምህርቱ ይዘት ጋርመጣጣሙ ከተረጋገጠ በኋላ፤ ለተማሪዎች ይሰጣል፡፡
ፈተናው
የሚሰጠው በሁለት መንገድ ነው፡፡ የመጀመርያው መንገድ፤ ተማሪዎች እዚያው ክፍል ውስጥ የሚጨርሱት የክፍል ፈተና ነው፡፡ ሁለተኛው
መንገድ ደግሞ ተማሪዎች እቤት ወስደው ከወላጆቻቸው ጋር ይሚሰሩት፤ እቤት የሚወሰድ ፈተና ሲሆን ዓላማውም የወላጆችን ተሳትፎ ለመመዘን
ነው፡፡
የፈተናው
ይዘት፤ እንደ ተማሪዎቹ የክፍል ደረጃ ቢለያይም፤ ጥያቄዎቹ የሚያተኩሩት ግን በ ሁለት የትምርት ዘርፎች ላይ ይሆናል፡፡ 1ኛ. የአማርኛ
ቋንቋ ማለትም (ፊደል፤ ንባብ፤ ጽሑፍ፤ ንግግር) 2ኛ. የሃይማኖት ትምህርት ማለትም (እምነት፤ ሥርዓት እና መዝሙር)
እንደተለመደው፤
ፈተና የሚሰጠው የተማሪዎችን እውቀት ለመመዘን ቢሆንም፤ በደብሩ የሚሰጠው ፈተና ግን ከዚህ በላይ ተጨማሪ ግቦች አሉት እነርሱም፡
- በትምህርት ቤቱ፤ ወጥ የሆነ እና የተቀናጀ የፈተና እና የምርቃት ሥርዓት ባሕል መጀመር
- የሥርዓተ ትምህርቱን ውጤታማነት መገምገም
- ወላጆች በማስተማር ሂደት ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ መመዘን ነው፡፡
የፈተናው
ውጤት፤ ለተማሪዎቹ ወላጆች የሚላክ ሲሆን፤ የውጤት ማሳወቂያው የሚይዘው የተማሪዎቹን የፈተና ውጤት፤ የክፍል አቴንዳንስ እና የመምህራኑን
አስተያየት ነው፡፡ ናሙናውን ለማየት ይህንን ይጫኑ፡፡
Sunday, February 24, 2013
ለመምህራን የድረ ገጽ ማኔጅመንት ሥልጠና ተሰጠ
ለሠልጣኞቹ
የተሰጡ ሁለት መማርያ ወረቀቶች ነበሩ፡፡ 1ኛ፡-ለሥልጠናው ዕለት ተዘጋጅተው መምጣት ያለባቸውን ጉዳዬች የሚያብራራ ወረቀት ሲሆን
ሁለተኛው ደግሞ በስድስት ክፍለ ትምህርቶች የተከፋፈለ የትምህርት
ወረቀት ነው፡፡ የትምህርት ወረቀቱን ለማየት ይህንን ይጫኑ፡፡
ይህንን
የድረ ገጽ ማኔጅመንት ሞያ የቀሰሙት መምህራን፤ በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ፤ በየክፍላቸው የሚያስተምሩትን ትምህርቶች፤ በዚህ ድረ ገጽ
ዓምዶች ላይ መለጠፍ ይጀምራሉ፡፡
ይሄ
ሥልጠና፤ ለመምህራን ከሚሰጡ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናዎች አንዱ ሲሆን፤ ወደፊት በዚህ ስልጠና ላልተሳተፉ መምህራን እና አገልጋዬች፤
ሌሎች ተዛማጅ የኮምፒውተር እና የሥርዓተ ትምህርት አተገባበር ሥልጠናዎች ይሰጣሉ፡፡
Thursday, February 21, 2013
ማስታወቂያ
ባለፈው ሳምንት የንባብ ክፍል ተማሪዎች ከመደበኛዉ ስርኣተ ትምህርቱ ያላገኙትን ለማካካስ እንዲመች ተማሪዎች እስካሁን ያሉትን መልመጃዎች እንዲጨርሱ ወላጆች ይረዷችዉ ዘንድ በኣክብሮት እንጠይቃለን።
ከንባብ ክፍል
Subscribe to:
Posts (Atom)


