Saturday, December 12, 2015

ወንበር ክፍልንም፤ አስተሳሰብንም ይለውጣል



በ ናዖድ ቤተሥላሴ
ለሁሉም ጊዜ አለው እንዲል መጽሐፉ፤ ቤተክርስቲያናችን እና ወላጆች ለልጆቻችን ትምህርት ቤት እንዲሟላ ከሚፈልጉት እና ከሚመኙት ነገሮች አንዱ የሆነው የመማርያ ወንበር ጉዳይ በአብዛኛው ተቃለለ።


በዚህ ዲሴምበር ውስጥ፤ ትምህርት ቤቱ ከቤተክርስቲያን አስተዳደር ባገኘው የአስቸኳይ ጉዳይ ብድር 120 (አንድ መቶ ሃያ) ወንበሮችን ለመግዛት ችሏል። ግዢው በአስቸኳይ ጊዜ ብድር የተከናወነው የወንበሮቹን ግዢ የት/ቤቱ አስተዳደርም ሆን የቤተክርስቲያኑ አስተዳደር በዚህ ዓመት እቅዳቸውም  በጀታቸው ይዘውት ስላልነበረ ነው። ግዥውን አስቸኳይ ያደረገውም ወንበሮቹ ዲሴምበር መጨረሻ በሚጠቃለል ታላቅ ቅናሽ ላይ በመቅረባቸው ነው።
አዲሶቹ ወንበሮች በአሁኑ ሰዓት ለመማሪያ ክፍሎቹም ሆን ለተማሪ ልጆቻችን ግርማ ሞገስን ሰጥተው፤ ለት/ቤቱ እና ለቤተክርስቲያኑም አስተዳደር ተስፋ ያለው የአገልግሎት ግብብነት እና ቅንነት መታሰቢያ ሃውልት ሆነው በየክፍሎቹ ተደርድረዋል።
እግር ጥሎት የመማርያ ክፍሎቹን የጎበኝ ወላጅም ሆን ካህን የሚያሳዩት መደሰት በራሱ ደስታ ይፈጥራል። ጎብኝዎች ታዲያ ከደስታቸው በኃላ ይሚናገሩት ቃላት ወንበሮቹ በሚያያቸው ላይ ሁሉ የአስተሳሰብ ለውጥ እያመጡ እንደሆነም ነው። ማስረጃ፦
1.      ሳይለመኑ ለወንበሮች ግዢ ሒሳብ ማወራረጃ የሚሆን የገንዝብ መዋጮ ይሰጣሉ ወይ ቃል ይገባሉ
2.      ካህናቶችም ለልጆቻችን ተጨማሪ አገልግሎት ሊሰጡ ቃል ይገባሉ (ለዚህም እነሆ በቅዳሴ ሰዓት ልጆቻችን በመማርያ ክፍሎች ሳሉ የማዕጠንት ቡራኬ ይደረግላቸው ጀምሯል)
3.      ነባር አገልጋዮች በግል እና በጋራ ሊያደርጓቸው የሚመኙትን ሃሳብ «ከእግዚአብሔር ጋር እንችላለን» በሚል መንፈስ ማሰማት ጀምረዋል
4.      አንዳንድ ግለሰቦች ጋር የነበረ «አስተዳደሮች እሺ አይሉም፤...» ወዘተ የሚል ስጋት እና ሰበብ ከአንደበታቸው ጠፍቶ ወድ «እንጠይቅ» እና «እናድርግ» ባይነት ሲሸጋገሩ አስተውያለሁ።
አዲሶቹ ወንበሮች ግን እንከን የላቸውም ማለት አይቻልም። ተማሪዎችም ሆነ አስተማሪዎች የተስማሙበት አንዱ እንከን የደብተር/ፎልደር ማስቀመጫ ኪስ ወይም ቦታ አለመኖር ነው። ለዚህ መፍትሔ የሚሆን መላዎችም በአስተዳደርም ሆን በግለሰቦች ዘንድ እየተብላሉ ናቸው። ወጪ ቆጣቢ መላ ካታያችሁ ጠቁሙን።
ሌላው እንከን ወንበሮቹ በምቾት ሲያገለግሉ የታየው እድሜያቸው ከ6 -13 ለሚደርሱ ተማሪዎች መሆኑ ነው። ለዚህም የተሻለ ጥናት እና መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ፤ ዕድሚያቸው ከ6 በታች ለሆኑ ተማሪዎቻችን በድሮዎቹ ወንበሮች እንዲገለገሉ ትተናችዋል (ከሃዘን ጋር)። የተሻለ መፍትሔ ካላችሁ ጠቁሙን።

ወንበሮቹን የገዛነው ከ እዚህ ነው ፤ ቅናሹ ሳያልፍ ሞክሩ።https://www.schooloutfitters.com/catalog/product_family_info/pfam_id/PFAM41827

ምስጋና ወ ወቀሳ ለየቀድሞዎቹ ጠርጴዛና ወንበሮች
 ይድረስ ለ ቀድሞ ወንበሮቻችን እና ጠረጴዛዎች።
በጊዜያችሁ ልጆቻችንን በትዕግስት ችላችሁ፤ ድንቅ አገልግሎት ሰለሰጣችሁን የእናንተንም ሆነ ወደ እኛ ያመጧችሁን በጎ አድራጊዎች ውለታ እግዚአብሔር ይቁጠርላችሁ። አሁንም ቢሆን ወይ ገንዝብ ወይ ልዩ አገልግሎት የመስጠት እድል ታገኙ ዘንድ ስቶር  በክብር አስቀምጠናችኋል።
ቢሆንም! ቢሆንም!  ድሮም አመጣጣችሁ ከየትምህርት ቤቱ አገልግሎታችሁን ጨርሳችሁ እኛ ላይ የተጣላችሁ ስለሆናችሁ ጎድታችሁንም ነበር።
  • 1ኛ   )   እኛን ወላጆችን፤ ለልጆቻቸው አዲስ ነገር መግዛት የማይችሉ የኔቢጤ አስመስላችሁን ነበር::
  • 2ተኛ)   በቤተክርስቲያን አስተዳደር ዘንድ የልጆች አገልግሎት «ትምህርት ቤት» በሚል ማዕረግ ታስቦ፤ በቂ በጀት እና ትኩረት እንዳላገኘ ላያችሁ ሁሉ እያሳበቃችሁ ስታሳቅቁን ነበር።
  • 3ተኛ)   ልጆቻንንም ያለ እድሚያቸው አስረጅታችሁ ተማሪ ሳይሆን ተጧሪ አስመስላችሁብንም ነበር ባይ ነኝ።
ይሄ ጉዳታችሁ የተገለጠልኝ መቼ እንደሆን ታውቃላችሁ! አዲሶቹ ወንበሮች ለጋ ልጆቻችንን በ «ወንበራዊ ፈገግታ» ፈገግ ብለው ሲያገልግሉ ባየሁ በመጀመርያው ቀን ነው።

አንባብያን ሆይ! «ወንበራዊ ፈገግታ» ምን ማለት እንደሆን ለመግለጥ ቃላት የለኝም። ለማወቅ ከፈለጋችሁ ግን መጀመርያ  በአዘቦት ቀን ኑ ና ባዶ ክፍል ተደብረው እዩዋቸው። ከዚያ ደግሞ እሁድ ኑና እዩዋቸው ወንበሮቹ ፈገግ  ብለው ታያላችሁ። ወንበሮቹ ሁሉ፤ ሁል ጊዜ ልጆች እንዲቀመጡባቸው የሚፈልጉ ይመስለኛል።

No comments:

Post a Comment

እናመሰግናለን፡፡ተሳትፎዎን ይቀጥሉ፡፡

blessing

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡.......In The Name of The Father, The Son and The Holy Spirit. Amen.

Amen

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን::