ስለ ላይብረሪው….
·
የላይብረሪያኗ(ኑ) ኃላፊነቶች
a. መጽሐፍትን እና ቁሳቁሶችን መዝግቦ
በሥርዓት መዝግቦ ማስቀመጥ
b. አዳዲስ መጽሐፍትን ለተማሪዎች እና
ወላጆች ማስተዋወቅ
c. ለወላጆሚዘጋጁ ትምህርታዊ መጽሔቶችን
ማሰራጨት
d. ለመምህራን እና ወላጆች ማዋስ
e. የተዋሱ ሰዎች ዕቃዎችን በሰዓቱ
እንዲመልሱ ማሳሰቢያ መላክ (ስልክ፤ኤሜይል፤ቴክስት)
f. ለጠፉ እቃዎች የሚሰበሰቡ ክፍያዎችን
ካሉ፤ በቤተክርስቲያን ገንዘብ ያዥ በኩል በደረሰኝ እንዲገቡ ማድረግ
·
መዋስ የሚችሉ እነማን ናቸው
a.
መምህራን
b. መደበኛ ተማሪ እንደሆኑ የተረጋገጠላቸው ተማሪዎች
c. ወላጆቻቸው የአገልግሎት ፎርም አጠናቀው የሞሉ
d. የሚዋሱ ሰዎች ስልካቸውን ወይም
ኢሜይላቸውን ማስመዝገብ ግዴታቸው ነው፡፡
·
የጊዜ ገደብ
a. መጽሐፍት የሚዋሱት ለ1-2 ሳምንት ነው
b. መምህራን ለተማሪዎቻቸው የሚሰጡት
የተለየ የጊዜ ገደብ ካለም ተቀባይነት አለው
·
የጠፉ፤ የተሰበሩ፤ የተበላሹ ዕቃዎች
a. የተዋሱ ሰዎች፤ የተዋሱት ዕቃ ቢጠፋባቸው
ምትኩን መግዛት ወይም መግዣ ገንዘቡን መክፈል አለባቸው
·
ልገሳ
a. ለልጆች ቋንቋ እና ሃይማኖ ማስተማርያ የሚጠቅሙ መጽሐፍትን እና ዕቃዎችን ለመለገስ
ያሰበ ሰው፤ ዕቃዎቹን ከማምጣቱ በፊት ላይብረሪኗን (ወ/ሮ
የወይንሸትን) ወይም አስተባባሪዎችን አግኝቶ ናሙናውን ማሳየት አለበት፡፡
·
የላይብረሪ ቦታ
a. ላይብረሪው በማስተባባሪያ ጽሕፈት ቤት ውስጥ ይገኛል
b. የሚሰጠውን አገልግሎት የማዋስ አገልግሎት ብቻ ነው (ልዩ የማንበቢያ ቦታ የለውም)
Well done please keep up the good work
ReplyDelete