Showing posts with label News. Show all posts
Showing posts with label News. Show all posts

Monday, August 5, 2013

የላይብረሪ አገልግሎት ጅምር

ለአዳጊ ልጆች ትምህርት እና ዕድገት የሚሆኑ ጥቂት የቋንቋ እና ሃይማኖት መማርያ መጽሐፍት፤ እና ቁሳቁሶች በአዳጊዎች ትምህርት ክፍል ይገኛሉ፡፡ ያሉትን የላይብረሪ ሀብቶች ለመጠቀም፤ የሚመጡትንም ለማስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የምትሰጠው ወ/ሮ ወይንሸት ናት፡፡
 
በቀጣይ ሳምንታት ውስጥም ለወላጆች ስለ ላይብሪው አጠቃቀም መሠረታዊ ሕጎች የሚገልጽ ደብዳቤ የሚላክላቸው ሲሆን፤ ወላጆች ላይብረሪውን ለመጠቀምም ሆነ ለማጠናከር ማድረግ ስለሚፈልጉት እገዛ እና ልገሳ፤ ወ/ሮ ወይንእሽትን እንዲያነጋግሩ እንጠይቃለን፡፡

Thursday, March 7, 2013

የመጀመርያ ሩብ ዓመት ፈተና ይሰጣል

News Report posted by Hanna

በዚህ በያዝነው ወር (ማርች 2013) መጨረሻ ሳምንት ላይ፤ በደብሩ የአዳጊዎች ትምህርት ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች በሙሉ የመጀመርያ ሩብ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል፡፡ ፈተናው የሚዘጋጀው በየክፍሉ በሚያስተምሩ መምህራን ሲሆን፤ ፈተናው ከሥርዓተ ትምህርቱ ይዘት ጋርመጣጣሙ ከተረጋገጠ በኋላ፤ ለተማሪዎች ይሰጣል፡፡

ፈተናው የሚሰጠው በሁለት መንገድ ነው፡፡ የመጀመርያው መንገድ፤ ተማሪዎች እዚያው ክፍል ውስጥ የሚጨርሱት የክፍል ፈተና ነው፡፡ ሁለተኛው መንገድ ደግሞ ተማሪዎች እቤት ወስደው ከወላጆቻቸው ጋር ይሚሰሩት፤ እቤት የሚወሰድ ፈተና ሲሆን ዓላማውም የወላጆችን ተሳትፎ ለመመዘን ነው፡፡

የፈተናው ይዘት፤ እንደ ተማሪዎቹ የክፍል ደረጃ ቢለያይም፤ ጥያቄዎቹ የሚያተኩሩት ግን በ ሁለት የትምርት ዘርፎች ላይ ይሆናል፡፡ 1ኛ. የአማርኛ ቋንቋ ማለትም (ፊደል፤ ንባብ፤ ጽሑፍ፤ ንግግር) 2ኛ. የሃይማኖት ትምህርት ማለትም (እምነት፤ ሥርዓት እና መዝሙር)

እንደተለመደው፤ ፈተና የሚሰጠው የተማሪዎችን እውቀት ለመመዘን ቢሆንም፤ በደብሩ የሚሰጠው ፈተና ግን ከዚህ በላይ ተጨማሪ ግቦች አሉት እነርሱም፡
 
  1. በትምህርት ቤቱ፤ ወጥ የሆነ እና የተቀናጀ የፈተና እና የምርቃት ሥርዓት ባሕል መጀመር
  2. የሥርዓተ ትምህርቱን ውጤታማነት መገምገም
  3. ወላጆች በማስተማር ሂደት ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ መመዘን ነው፡፡

የፈተናው ውጤት፤ ለተማሪዎቹ ወላጆች የሚላክ ሲሆን፤ የውጤት ማሳወቂያው የሚይዘው የተማሪዎቹን የፈተና ውጤት፤ የክፍል አቴንዳንስ እና የመምህራኑን አስተያየት ነው፡፡ ናሙናውን ለማየት ይህንን ይጫኑ፡፡

በሥርዓተ ትምህርቱ መሰረት፤ የሚቀጥሉት የሁለተኛው፤ የሦስተኛው፤ እና የአራተኛው ሩብ ዓመት መመዘኛ ፈተናዎች የሚሰጡት በ June, September and December ወራት መጨረሻ ሳምንታት ውስት ነው፡፡

 
 

Thursday, February 14, 2013

የድረ-ገጽ ማኔጅመንት ሥልጠና ይሰጣል



የአዳጊ ልጆችን በማስተማር እና በማስተባበር ላይ ለሚገኙ መምህራን እና አገልጋዬች፤ የድረ-ገጽ ማኔጅመንት ሥልጠና ይሰጣል፡፡ የሥልጠናው ዓላማ፤ መምህራን እና አስተባባሪዎች፤ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ሳምንታዊ ትምህርቶችን እና መልዕክቶችን እንዲለጥፉ ማስቻል ነው፡፡
ሥልጠናው ሊሰጥ የታቀደው እሁድ ጃንዋሪ 24፤ 2013፤ ከሥርዓተ ቅዳሴ በኋላ ባለው ሰዓት ሲሆን፤ ሥልጠናው በጠቅላላው 4 ሰዓታት ይፈጃል፡፡ የሥልጠናውም ዋና ይዘት፤ መምህራን በዚህ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ ጽሑፍ፤ ስዕል እና ቪዲዬ የሚለጥፉበትን ቴክኒክ ማሳየት ሲሆን፤ በተዛማጅም፤  የድረ ገጹን የሚመለከቱ ጉዳዬች ላይ ሀሳብ እና አስተያየት ይሰበሰባል፡፡
በሥልጠናው ወቅት፤ እያንዳንዱ ሰልጣኝ፤ የራሱን ላፕቶፕ ኮምፒውተር የሚጠቀም ሲሆን፤ የስልጠናው አዘጋጆችም ለሰልጣኞች የተዘጋጁ የሥልጠና ወረቀቶችን ይሰጣሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፤ እያንዳንዱ ሠልጣኝ፤ የተዘጋጁ ትምህርታዊ ጽሑፎችን በድረ ገጾች ላይ በመለጠፍ፤ ተግባራዊ ልምምድ ያደርጋል፡፡
ይህ ሥልጠና፤ የአዳጊ ልጆች መምህራንን ቴክኒካዊ ብቃት ለመጨመር ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ ሲሆን፤ በቀጣይም ሌሎች የቡድን እና የግል ሥልጠናዎች ይደረጋሉ፡፡

blessing

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡.......In The Name of The Father, The Son and The Holy Spirit. Amen.

Amen

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን::