Monday, April 1, 2013

የሩብ ዓመት ፈተና ተሰጠ

መምህራን የትምህርት ዘዴያቸውን ውጤታማነት የሚገመግሙበት፤ ወላጆች ልጆቻቸው መማር አለማማራቸውን የሚያረጋግጡበት አንዱ መንገድ ፈተና መስጠት ነው፡፡ የአዳጊዎች ትምህረት ክፍልም ማርች 31 ቀን 2013፤ በሥሩ ለሚማሩ ከ150 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የአንደኛ ሩብ ዓመት ፈተና ሰጠ፡፡
 
ፈተናው የአማርኛ ቋንቋ እና የሃይማኖታዊ እውቀትን ለመመዘን የተዘጋጀ ሲሆን፤ የተሰጠውም በሁለት አይነት መንገድ ነው፡፡ 1ኛ በክፍል ውስጥ ፈተና 2ኛ እቤት በሚወሰድ ፈተና፡፡
የክፍል ውስጥ ፈተናው፤ የቡድን እኛ የግል ጥያቄዎችን ያጠቃለለ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተማሪ ያለበትን ትክክለኛ የእውቀት ደረጃ ለመመዘን ይረዳል በሚል እሳቤ የተደረገ ነው፡፡ እቤት የሚወሰደው ፈተና ዋና አላማ፤ ወላጆች ልጆቻቸውን በማስተማር ያላቸውን ተሳትፎ ለመመዘን ሲሆን፤ ጥያቄዎቹ የተዘጋጁትም ተማሪዎቹ የወላጆቻቸውን እርዳታ ካላገኙ በቀር በግል ለመስራት እንዲቸገሩ ታስቦ ነው፡፡ ልጆቹ እቤት በወሰዱት ፈተና የሚያገኙት ውጤት፤ የወላጆቹ የድጋፍ መጠን መለኪያም የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡
በሚቀጥሉት ሳምንታትም ውስጥ ሁለት ዋና ዋና ተግባራት እንደሚከናወኑ ይጠበቃል፡፡
  1. የተማሪዎችን ምዘና ውጤት ለወላጆች ማሳወቅ የመጀመርያው ሥራ ሲሆን፤ ለሁሉም ተማሪዎች ወጥ የሆነ ፎርማት ያለው የፈተና ሪፖርት ማድረጊያ ቅጽ እየተዘጋጀ ነው፡፡
  2.  
  3. መምህራኑ እና አስተባባሪዎች ፈተናውን በተመለከተ የጋራ ውይይት ያደርጋሉ፡፡ በውይይቱም፤ መምህራኑ የፈተናውን አዘገጃጀት እና አሰጣጥ ሥርዓት በተመለከተ ስኬቶችን እና ድክመቶችን መዝነው፤ ለወደፈቱ የሚጠቅሙ ማሻሻያ እና ማስተካከያ መላዎችን እንዲቀይሱ ይጠበቃል፡፡
 

No comments:

Post a Comment

እናመሰግናለን፡፡ተሳትፎዎን ይቀጥሉ፡፡

blessing

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡.......In The Name of The Father, The Son and The Holy Spirit. Amen.

Amen

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን::