Thursday, March 7, 2013

የመጀመርያ ሩብ ዓመት ፈተና ይሰጣል

News Report posted by Hanna

በዚህ በያዝነው ወር (ማርች 2013) መጨረሻ ሳምንት ላይ፤ በደብሩ የአዳጊዎች ትምህርት ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች በሙሉ የመጀመርያ ሩብ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል፡፡ ፈተናው የሚዘጋጀው በየክፍሉ በሚያስተምሩ መምህራን ሲሆን፤ ፈተናው ከሥርዓተ ትምህርቱ ይዘት ጋርመጣጣሙ ከተረጋገጠ በኋላ፤ ለተማሪዎች ይሰጣል፡፡

ፈተናው የሚሰጠው በሁለት መንገድ ነው፡፡ የመጀመርያው መንገድ፤ ተማሪዎች እዚያው ክፍል ውስጥ የሚጨርሱት የክፍል ፈተና ነው፡፡ ሁለተኛው መንገድ ደግሞ ተማሪዎች እቤት ወስደው ከወላጆቻቸው ጋር ይሚሰሩት፤ እቤት የሚወሰድ ፈተና ሲሆን ዓላማውም የወላጆችን ተሳትፎ ለመመዘን ነው፡፡

የፈተናው ይዘት፤ እንደ ተማሪዎቹ የክፍል ደረጃ ቢለያይም፤ ጥያቄዎቹ የሚያተኩሩት ግን በ ሁለት የትምርት ዘርፎች ላይ ይሆናል፡፡ 1ኛ. የአማርኛ ቋንቋ ማለትም (ፊደል፤ ንባብ፤ ጽሑፍ፤ ንግግር) 2ኛ. የሃይማኖት ትምህርት ማለትም (እምነት፤ ሥርዓት እና መዝሙር)

እንደተለመደው፤ ፈተና የሚሰጠው የተማሪዎችን እውቀት ለመመዘን ቢሆንም፤ በደብሩ የሚሰጠው ፈተና ግን ከዚህ በላይ ተጨማሪ ግቦች አሉት እነርሱም፡
 
  1. በትምህርት ቤቱ፤ ወጥ የሆነ እና የተቀናጀ የፈተና እና የምርቃት ሥርዓት ባሕል መጀመር
  2. የሥርዓተ ትምህርቱን ውጤታማነት መገምገም
  3. ወላጆች በማስተማር ሂደት ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ መመዘን ነው፡፡

የፈተናው ውጤት፤ ለተማሪዎቹ ወላጆች የሚላክ ሲሆን፤ የውጤት ማሳወቂያው የሚይዘው የተማሪዎቹን የፈተና ውጤት፤ የክፍል አቴንዳንስ እና የመምህራኑን አስተያየት ነው፡፡ ናሙናውን ለማየት ይህንን ይጫኑ፡፡

በሥርዓተ ትምህርቱ መሰረት፤ የሚቀጥሉት የሁለተኛው፤ የሦስተኛው፤ እና የአራተኛው ሩብ ዓመት መመዘኛ ፈተናዎች የሚሰጡት በ June, September and December ወራት መጨረሻ ሳምንታት ውስት ነው፡፡

 
 

1 comment:

እናመሰግናለን፡፡ተሳትፎዎን ይቀጥሉ፡፡

blessing

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡.......In The Name of The Father, The Son and The Holy Spirit. Amen.

Amen

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን::