ጓዝ ጠቆሎ፤ ከዋሽንግተን ዲ.ሲ ወደ አትላንታ መሄድ በራሱ ከባድ ቢሆንም፤ ለመምህር የሻነው ግን በጣም የከበደው፤ በሃይማኖት ኮትኩቶ ያሳደጋቸው ተማሪዎቹን ትቶ መሄድ ነው፡፡ ስለዚህም፤ ዛሬ በደብሩ የአዳጊዎች ትምህርት ክፍል በተደረገለት መጠነኛ የሽኝት ስጦታ ስነስርዓት ላይ፤ መምህር የሻነው ያደረገው ስጦታችንን መቀበል ብቻ አይደለም፤ ላስተማራቸው ተማሪዎች፤ የውዳሴ ማርያም የጸሎት መጽሐፍ ስጦታ እና የ ‹‹ቅዳሴ ተማሩ›› አደራም በመስጠትም እንጂ፡፡
በዚህ አጋጣሚም ወንድማችን፤ በሄደበት ሁሉ እግዚአብሔር እንዲጠብቀው፤ መንገዱ እንዲቃናለት እና የሚወደውንም የልጆ አገልግሎት በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ከልብ እንመኛለን፡፡
በስንብት ንግግሩም በድጋሚ እንዳረጋገጠልን፤ ወንድማችን በድረገጻችን ላይ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን እና ትምህርቶች በመለጠፍ፤ እንዲሁም ለተወጠነውን የማስተማርያ መጽሐፍ ዝግጅት የሚሆኑ ሀሳቦችን በመለገስ የተልዕኮ አገልግሎቱን ይሰጠናል፡፡
No comments:
Post a Comment
እናመሰግናለን፡፡ተሳትፎዎን ይቀጥሉ፡፡