ይህ ድንቅ ልጅ የሚሰራቸውን የእደ ጥበብ ውጤቶች የሚያይ ሰው በሁለት ነገር ይገረማል፤ 1ኛ. ልጁ
በሚሰራቸው የእደ ጥበብ ስራዎች ጥራት 2ኛ. በልጁ የመጠሪያ ስም እና ግብር መጣጣም፡፡
ስሙ በኪነ ጥበቡ አየለ ይባላል፡፡ በደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርርስቲያን የመሠረተ ሃይማኖት
ክፍል ተማሪ ነው፡፡ በኪነ ጥበቡ ካለው ጨዋ ስነምግባር እና የቤተክርስቲያን ፍቅር በተጨማሪ፤ ኢትዬጵያዊ ባሕሉን እና ታሪኩን የሚያንጸባርቁ
የእደ ጥበብ ስራዎችን ይሰራል፡፡
![]() |
በኪነጥበቡ አየለ ከጥበብ ሥራዎቹ ጋር |
![]() |
በኪነጥበቡ አየለ እና ዘማሪ የሻነው መኮንን |
በፎቶግራፉ ላይ እንደምታዩት፤ የሰራው ሞዴል፤ ‹‹የልጅ ሥራ›› አይመስልም፡፡ በቅርጹ ተመጣጣኝነት፤ በክሮቹ አደራደር እና አቆጣጠር ረቂቅነት፤ በሞዴሉ ጥንካሬ እና ሞዴሉን ለመስራት በተጠቀመባቸው ጥሬ እቃዎች እንደሚንጻባረቀው፤ የኪነጥበቡ ሥራ የጥበበኛ ሥራ ነው፡፡
የኪነ
ጥበቡን ሥራዎችን መነሻ በማድረግ፤ የደብሩ አዳጊዎች ክፍል፤ ወደፊት፤ በአዳጊዎች የተሰሩ ተመሳሳይ የእደ ጥበብ እና ፈጠራ ውጤቶችን ለምዕመናን የሚያሳይበት፤
ለሌሎች ልጆችም ማስተማርያ የሚያውልበት መላ እንደሚፈልግ ይጠበቃል፡፡
No comments:
Post a Comment
እናመሰግናለን፡፡ተሳትፎዎን ይቀጥሉ፡፡