አዳጊ ልጆች መዝሙራትን ማጥናት ብቻ ሳይሆን፤ ስለ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙርም መሰረታዊ እውቀት እንዲኖራቸው
የሚያደርግ የመዝሙር መማርያ መጽሔት ዝግጅት ተጀምሯል፡፡ ዝግጅቱ የሚመራው በሰንበት ትምህርትቤት ውስጥ በመዘምራንነት በምታገለግለው ዘማሪት
ቀጸላ ነው፡፡
የመማርያ መጽሔቱ ይዘት የሚከተለውን እንዲመስል የታሰበ ሲሆን፤ ጽሑፉ በቤተክርስቲያን መምህራን ታርሞ
ሲጸድቅ፤ ልጆቹ እንዲማሩበት የሚደረግ ይሆናል፡፡መጽሔቱ መግለጫ
ስዕላትን የሚይዝ ሲሆን፤ በተቻለ መጠንም የእንግሊዝኛ ትርጉምም እንዲኖረው ይሞከራል፡

ይዘት
·
ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ምንድን ነው?
·
የቅዱስ ያሬድ ታሪክ
·
የመዝሙር መገልገያዎች
·
የተመረጡ መዝሙሮች
o ለንባብ
ክፍል
o ለመሠረተ
ሃይማኖት ክፍል
o ለዓምደ
ሃይማኖት ክፍል
·
ጥያቄ እና መልሶች
መጽሔቱ በጃንዋሪ 2013 የሚጀመር ሲሆን በሁለት
ወር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡
No comments:
Post a Comment
እናመሰግናለን፡፡ተሳትፎዎን ይቀጥሉ፡፡