ዛሬ እሁድ ጃንዋሪ 13 2013፤ በአዳጊዎች ትምህርት አገልግሎት ክፍል የተጠናቀቁ፤ የተጀመሩ እና ተስፋ የተገኘባቸው አያሌ ነገሮች ተከናውነዋል፡፡
1ኛ. ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡ የአለፈው ዓመት፤ በመምህር ካሰኝ ማብረጃ እና በመምህር የሻነው መኮንን ፤ የአማርኛ ቋንቋ እና የሃይማኖት ትምህርት ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎች በአባቶች ቡራኬ እና ጸሎት ተመርቀዋል፡፡
1ኛ. ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡ የአለፈው ዓመት፤ በመምህር ካሰኝ ማብረጃ እና በመምህር የሻነው መኮንን ፤ የአማርኛ ቋንቋ እና የሃይማኖት ትምህርት ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎች በአባቶች ቡራኬ እና ጸሎት ተመርቀዋል፡፡
2ኛ. የጀማሪ ተማሪዎች ክፍል ተከፍቷል፡፡ ይህ አዲስ ክፍል የተከፈተው፤ በጊዜያዊነት፤ በቤተክርስቲያኑ አዳራሽ መድረክ ላይ ሲሆን፤ የማስተማርያ መንገዱም በኦቨር ሄድ ፕሮጀክተር ነው፡፡ ክፍሉን በዋና አስተባባሪነት የሚመሩት መምህር ሲሳይ ግዛቸው ነው፡፡
3ኛ. የመልካም ልደት ካርድ መላክ ተጀመሯል፡፡ በዚህ ጃንዋሪ ወር ውስት፤ ልደታቸውን ለሚያከብሩ ተማሪዎቻችንን፤ የመምህራን ፊርማ ያለበት የቤተክርስቲያን ፖስት ካርድ በቤት አድራሻቸው ተልኮላቸዋል፡፡ ይህም የፖስታ መልዕክት አገልግሎት፤ ወደፊት፤ ፖስት ካርድ ከመላክ አልፎ ወላጆች በየቤታቸው ለልጆቻቸው የሚሆኑ ትምህርቶችን የሚያገኙበትም መንገድ እንደሚሆን ተስፋ ይደረጋል፡፡
![]() |
በኦቨር ሄድ ፕሮጀክተር ፊደል ሲታይ (ካሜራዬ
ሰነፍ ሆኖ እንጂ፤ ቤቱ ጨለማ አይደለም)
|
4ኛ. ጠቃሚ ፕሮፌሽን ያላቸው ወላጆች አገልግሎቱን ተቀላቅለዋል፡፡ ይህም ትልቅ ተስፋ ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አርቲስት ወ/ሮ ፍቱን ለአዳጊዎች ለሚዘጋጁ መጽሔቶች እና መጽሐፍት ኢሉስትሬሽን ስዕሎች ለማዘጋጀት ፈቃደኝነታቸውን ገልጸው የመጽሔት ዝግጅት ፕሮጀክት ተቀብለዋል፡፡ በአማርኛ ታይፒንግ እና በማስተማር ሊረዱ የሚችሉ ፈቃደኛ ወላጆች (ወ/ሮ ሰናይት ጣሰው እና ወ/ሮ እናትዓለም)፤ እንዲሁም አዳጊዎቹን መዝሙር በማስጠናት እና የመዝሙር መማርያ መጽሔት በማዘጋጀት የሚረዱ ሰንበት ተማሪዎች (ዘማሪት መታሰቢያ ካሳ እና ዘማሪት ትርንጎ አበበ) ፈቃደኝታቸውን ገልጸዋል፡፡
No comments:
Post a Comment
እናመሰግናለን፡፡ተሳትፎዎን ይቀጥሉ፡፡