Tuesday, January 22, 2013

The Future is already here!

ዘጋቢ፡-ብሥራተ ገብርኤል

የወላጆች ጥረት በቤተክርስቲያን ተቋማዊ ዝግጅት ካልተደገፈ፤ በአንጻሩም የቤተክርስቲያን ዝግጅት በወላጀቾች መንፈሳዊ እና ቤተሰባዊ ጥረት ካልታገዘ፤  ልጆቻችን የያዙትን ይለቃሉ፤ ሲከፋም ስደተኞችን ለሚያጠቃው የማንነት ቀውስ አደጋ ይጋለጣሉ...ወዘተ እያልኩ ስለ ስለቤተክርስቲያን ተቋማዊ ዝግጅት በድጋሚ እንዳስብ ያደረገኝ ይሄ ልጅ ነው፡፡

 
  
ቀኑ ቃና ዘገሊላ ነውና፤ Jan 20, 2013፤ ውጪ፤ በቤተክርስቲያኑ ዓውደ ምህረት ላይ፤ ታቦተ ህጉ እየነገሰ ነው፡፡ ካህናትም ያሬዳዊ ዜማ እና ሽብሸባ እያቀረቡ ነው፡፡ ይሄ ልጅ ደግሞ


Wednesday, January 16, 2013

ማስታወቂያ




በሚቀጥለው እሁድ ጃንዋሪ 20 2013 የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡ ታቦተ ሕጉም ይወጣል፡፡ ስለዚህም በአዳራሹ መድረክ ላይ የተጀመረው፤ የጀማሪ ተማሪዎች ክፍል ትምህርት ላይኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ወላጆች እና መምህራን፤ የዕለቱን ሁኔታ አይተው፤ አስፈላጊውን የመርሐግብር ማስተካከያ ከወዲሁ እንዲያደርጉ ሰበካ ጉባዔው ያስታውቃል፡፡
ከአቶ ዮርዳኖስ ብርሃኑ

Monday, January 14, 2013

የሳምንቱ ክንውኖች እና ተስፋዎች

ዛሬ እሁድ ጃንዋሪ 13 2013፤ በአዳጊዎች ትምህርት አገልግሎት ክፍል የተጠናቀቁ፤ የተጀመሩ እና ተስፋ የተገኘባቸው አያሌ ነገሮች ተከናውነዋል፡፡

1ኛ. ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡ የአለፈው ዓመት፤ በመምህር ካሰኝ ማብረጃ እና በመምህር የሻነው መኮንን ፤ የአማርኛ ቋንቋ እና የሃይማኖት ትምህርት ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎች በአባቶች ቡራኬ እና ጸሎት ተመርቀዋል፡፡



የመርሃግብሩን ዝርዝር ሪፖርት እና ፎቶግራፎችን ለማየት፤ የመሠረተ ሃይማኖት ክፍልን ገጽ ይህን ሊንክ በመጫን ያንብቡ›››
2ኛ. የጀማሪ ተማሪዎች ክፍል ተከፍቷል፡፡ ይህ አዲስ ክፍል የተከፈተው፤ በጊዜያዊነት፤ በቤተክርስቲያኑ አዳራሽ መድረክ ላይ ሲሆን፤ የማስተማርያ መንገዱም በኦቨር ሄድ ፕሮጀክተር ነው፡፡ ክፍሉን በዋና አስተባባሪነት የሚመሩት መምህር  ሲሳይ ግዛቸው ነው፡፡
በኦቨር ሄድ ፕሮጀክተር ፊደል ሲታይ (ካሜራዬ ሰነፍ ሆኖ እንጂ፤ ቤቱ ጨለማ አይደለም)
3ኛ. የመልካም ልደት ካርድ መላክ ተጀመሯል፡፡ በዚህ ጃንዋሪ ወር ውስት፤ ልደታቸውን ለሚያከብሩ ተማሪዎቻችንን፤ የመምህራን ፊርማ ያለበት የቤተክርስቲያን ፖስት ካርድ በቤት አድራሻቸው ተልኮላቸዋል፡፡ ይህም የፖስታ መልዕክት አገልግሎት፤ ወደፊት፤ ፖስት ካርድ ከመላክ አልፎ ወላጆች በየቤታቸው ለልጆቻቸው የሚሆኑ ትምህርቶችን የሚያገኙበትም መንገድ እንደሚሆን ተስፋ ይደረጋል፡፡
4ኛ. ጠቃሚ ፕሮፌሽን ያላቸው ወላጆች አገልግሎቱን ተቀላቅለዋል፡፡ ይህም ትልቅ ተስፋ ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አርቲስት ወ/ሮ ፍቱን ለአዳጊዎች ለሚዘጋጁ መጽሔቶች እና መጽሐፍት ኢሉስትሬሽን ስዕሎች ለማዘጋጀት ፈቃደኝነታቸውን ገልጸው የመጽሔት ዝግጅት ፕሮጀክት ተቀብለዋል፡፡ በአማርኛ ታይፒንግ እና በማስተማር ሊረዱ የሚችሉ ፈቃደኛ ወላጆች (ወ/ሮ ሰናይት ጣሰው እና ወ/ሮ እናትዓለም)፤ እንዲሁም አዳጊዎቹን መዝሙር በማስጠናት እና የመዝሙር መማርያ መጽሔት በማዘጋጀት የሚረዱ ሰንበት ተማሪዎች (ዘማሪት መታሰቢያ ካሳ እና ዘማሪት ትርንጎ አበበ ፈቃደኝታቸውን ገልጸዋል፡፡

Wednesday, January 2, 2013

የመዝሙር መማርያ መጽሔት ዝግጅት ተጀምሯል


አዳጊ ልጆች መዝሙራትን ማጥናት ብቻ ሳይሆን፤ ስለ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙርም መሰረታዊ እውቀት እንዲኖራቸው የሚያደርግ የመዝሙር መማርያ መጽሔት ዝግጅት ተጀምሯል፡፡ ዝግጅቱ የሚመራው በሰንበት ትምህርትቤት ውስጥ በመዘምራንነት በምታገለግለው ዘማሪት ቀጸላ ነው፡፡
የመማርያ መጽሔቱ ይዘት የሚከተለውን እንዲመስል የታሰበ ሲሆን፤ ጽሑፉ በቤተክርስቲያን መምህራን ታርሞ ሲጸድቅ፤ ልጆቹ እንዲማሩበት የሚደረግ ይሆናል፡፡መጽሔቱ መግለጫ ስዕላትን የሚይዝ ሲሆን፤ በተቻለ መጠንም የእንግሊዝኛ ትርጉምም እንዲኖረው ይሞከራል፡



ይዘት
·         ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ምንድን ነው?
·         የቅዱስ ያሬድ ታሪክ
·         የመዝሙር መገልገያዎች
·         የተመረጡ መዝሙሮች
o   ለንባብ ክፍል
o   ለመሠረተ ሃይማኖት ክፍል
o   ለዓምደ ሃይማኖት ክፍል
·         ጥያቄ እና  መልሶች

መጽሔቱ በጃንዋሪ 2013 የሚጀመር ሲሆን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

blessing

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡.......In The Name of The Father, The Son and The Holy Spirit. Amen.

Amen

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን::