Monday, December 17, 2012

የዓምደ ሃይማኖት ክፍል ወቅታዊ ሁኔታ



በናዖድ ቤተሥላሴ

የዓምደ ሃይማኖት ክፍል ተማሪዎች፤ በአንጻራዊ ደረጃም ቢሆን ለብዙ ዓመታት ሲማሩ የቆዩ፤ በዕድሜያቸውም በሰለል ያሉ ናቸው፡፡ ስለዚህ፤ ከተለመደው የትምህርት ዘዴ በተጨማሪ፤ በግል እና በቡድን የሚሰሩዋቸውን የፈጠራ እና የጥናት ፕሮጀክቶች ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም የትምህርት ዘዴ ለዓምደ ሃይማኖ ክፍል በተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ተገልጧል፡፡

ለአደጊዎቹ የሚመጥን ፕሮጀክት ለመቅረጽ ግን መጀመርያ ተማሪዎቹ ያላቸውን ፍላጎት፤ ችሎታ፤ ሙያ እና ቁሳዊ አቅም ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህንንም ለማወቅ ዲሴምበር 15 ቀን ለተገኙት ተማሪዎች ቀላል መጠይቅ እንዲሞሉ ተደርጎ ነበር፡፡ (መጠይቁን ይመልከቱ)፡፡

በዚህ ሪፖርትም በመጠይቁ የተገኙ ቁምነገሮች እንደሚከተለው በአጭሩ ቀርበዋል፡፡



·         ከ80ፐርሰንት በላይ አዳጊዎች የአማርኛ ቋንቋ ይሰማሉ፤ ወይ ይናገራሉ፡፡ ይህ መረጃ፤ መምህራን አዳጊዎቹ በእንግሊዝኛ ለመግባባት መጣር እንደማያስፈልጋቸው፤ ይልቁንም ሁሉቱንም ቋንቋዎች እንደአስፈላጊነታቸው መቀላቀል እንደሚገባቸው የሚያመላክት ነው፡፡

·         ብዙዎቹ ተማሪዎች በቤተክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ በመዘምራንነት፤ በዲያቆንነት፤ ወዘተ ለማገልገል ፈቃደኛ ናቸው፡፡

·         ተማሪዎቹ የተለያየ ተሰጥኦ፤ ችሎታ እና ቁሳዊ አቅም እንዳላቸውም ታይቷል፡፡ የአዳጊዎች ትምህርት ክፍልም፤ በተሰበሰበውም መረጃ መሰረት፤ ተመሳሳይ ችሎታ እና አቅም ያላቸውን ተማሪዎች በቡድን አደራጅቶ፤ የሚመጥናቸውን ፕሮጀክት በመቅረጽ፤ ቤተክርስቲያናቸውን በሚችት አቃም እንዲጠቅሙ፤ ራሳቸውም እንዲጠቀሙ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

መረጃው በሚሰበሰብበት ጊዜ፤ በክፍሉ ውስጥ ይታይ የነበረው የመማር ማስተማር ዲሲፕሊን ግን መምህራን ሊመክሩበት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ ማየት ተችሏል፡፡ የአዳጊዎች ትምህርት ክፍል ወደፊት በሚያዘጋጀው የመምህራን ውይይት እና ሞያ ማጎልበቻ ሥልጠና ላይ የክፍል ሥነምግባር ስታንዳርድ ዝግጅት በአጀንዳነት እንዲያዝ ተደርጓል፡፡


ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን

2 comments:

  1. ናዖድ፤ ይህ መቸም በጣም ጥሩ ጅምር ነው። ቀደም ብሎ ብዙ ሄደውና የተለያዩ ፕሮጀክቶች ሰርተው ስለነበረ በዚያ ላይ build ማድረግ ኣለብን።

    ReplyDelete
    Replies
    1. you're right. That is how we can make a real progress.

      Delete

እናመሰግናለን፡፡ተሳትፎዎን ይቀጥሉ፡፡

blessing

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡.......In The Name of The Father, The Son and The Holy Spirit. Amen.

Amen

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን::