Monday, December 10, 2012

የሥ.ት. ትግበራ ቅድመ ዝግጅቱ ምን ይመስላል?

በናዖድ ቤተሥላሴ

ለደብሩ አዳጊ ልጆች ትምህርት የተዘጋጀው የሥርዓተ ትምህርት (ሥ.ት) ፕሮፖዛል፤ ወደ ተግባር እንዲውል በደብሩ ኃላፋች ከተፈቀደ በኋላ፤ የአዳጊ ክፍሉ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እና ቁሳዊ ዝግጅት ጀምሯል፡፡ ቅድመ ዝግጅቱ ሦስት መልክ ያለው ነው፡፡

የሥ.ት. ትግበራው ዋና ትኩረት የመጀመርያ ሩብ ዓመት (ጃንዋሪ፤ፌብሩዋሪ፤ማርች 2013) ሥርዓተ ትምህርት ነው፡፡ ይህ የመጀመርያ ሩብ ዓመት እንደ ፓይለት ፕሮጀክት (የሙከራ ፕሮጀክት) ሆኖ፤ በሩብ ዓመቱ መጨረሻ ላይ፤ የተገኙ ስኬቶች፤ ድክመቶች እና ጉድለቶች ተገምግመው፤ አስተዳደራዊም ስትራቴጂካዊም ለውጥ ይደረጋል፡፡

በዚህም መሰረት፤ እስካሁን የተከወኑ ተግባራት እነሆ፡-


1ኛ. አስተዳደራዊ ዝግጅት
የአዳጊ ክፍሉ ይሄ ነው የሚባል አስተዳደራዊ መዋቅር እና አደረጃጀት ስላልነበረው፤ በሚከተለው መልክ ተደራጅቶ፤ የክፍል ኃላፊዎችን ድልድል ጀምሯል (ለማየት click here)

ተማሪዎች፤ መምህራን እና ሌሎች የአዳጊ ክፍል አገልጋዬች መደበኛ የምዝገባ ፎርም እንዲኖራቸው ስለሚያስፈልግ፤ በቂ ፎርም ተዘጋጅቶ፤ ለተማሪዎች እና ለአገልጋዬች ታድሏል (ፎርሞቹን ለማየት Click here )፡፡ የፎርም መሙላቱ እንቅስቃሴ፤ በአንድ ዙር እንደማይሳካ ስለሚታወቅ፤ ጥረቱ በቀሩት የዲሴምበር እሁዶች ሁሉ ይቀጥላል

2ኛ. ቁሳዊ ዝግጅት
ሥርዓተ ትምህርቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዱ መሰረታዊ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ዝግጅት ተጀምሯል፡፡ የዝግጅቱ ዋና ትኩረት ግን፤ ለወላጆች የሚላክ ወርኃዊ የግብረ ገብ ትንሽ መጽሔት (Booklet) ማዘጋጀት ላይ) ነው፡፡

ለፊደል ቤት ተማሪዎች፤ የጥር ትምህርት መርሐግብር የሚሆን፤ አንድ ትንሽ መጽሔት ተዘጋጅቶ፤ ለቤተክርስቲያን መምህራን ተሰቷል፡፡ መምህራኑ፤ በመጽሔቷ ላይ የተጻፈውን ጽሑፍ እና ስዕላት ከቤተክርስቲያን ትምህርት አንጻር ገምግመው እና አስተካክለው ሲመልሱ፤ መጽሔቷ  ቢያንስ በ120 ኮፒ ተባዝታ፤ በጃንዋሪ ወር ውስጥ፤ በተማሪዎች በኩል ለወላጆች ትላካለች፡፡

በዚህ ዓይነትም ሌሎች ዘጠኝ (9) መጽሔቶች እና አንድ የፕሮጀክት ፎርማት ይዘጋጃሉ፡፡(የመጽሔት ናሙና ለማየት Click here)

3ኛ. የሰው ኃይል ዝግጅት
ከሥርዓተ ትምህርቱ ይዘት አንጻር፤ እስከ አሁን ድረስ በቂ መምህራን አልተገኙም፡፡ ስለዚህ ያሉትን ከሥርዓተ ትምህርቱ ጋር የማስተዋወቅ ሥራ መስራት እንደ ተጠበቀ ሆኖ፤ ተጨማሪ በጎ ፈቃደኛ መምህራን እና አገልጋዮችን ከሰንበት ትምህርትቤት እና ከወላጆች የማግኘት ጥረት ተጀምሯል፡፡

በቀሩት የዲሴምበር 2012 እሁዶች ውስጥ እንዲጠናቀቁ የታቀዱ ጉዳዮችም የሚከተሉት ናቸው፡፡
  1. ሁሉም ክፈሎች ቢያንስ አንድ መደበኛ የቋንቋ እና የሃይማኖት መምህር እንዲኖራቸው ማድረግ
  2. መምህራኑ ሥርዓተ ትምህርቱን ተመርኩዘው ወርኃዊ ትምህርቶችን እንዲያዘጋጁ ማድረግ
  3. መምህራን የትምህርት መርጃ መሳርያ ዝርዝር ጥያቄ እንዲያቀርቡ ማድረግ
  4. ለአንድ ሩብ ዓመት የሚበቃ የግብረ ገብ መጽሔቶች በደብሩ መምህራን አሳርሞ ለሕትመት ማዘጋጀት

 

No comments:

Post a Comment

እናመሰግናለን፡፡ተሳትፎዎን ይቀጥሉ፡፡

blessing

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡.......In The Name of The Father, The Son and The Holy Spirit. Amen.

Amen

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን::