Monday, December 24, 2012

ስንት ተማሪዎች ተመዘገቡ

እስከ ዛሬ ድረስ የምዝገባ ፎርም አሟልተው የተመዘገቡ ተማሪዎች መረጃ፡፡

የክፍል ደረጃ
የተማሪዎች ብዛት
 
 
ፊደል ቤት
16
ንባብ ቤት
42
መሰረተ ሃይማኖት
20
ዓምደ ሃይማኖት
37
ጠቅላላ
115

እኒህ ተማሪዎች እና ወደፊትም የሚመዘገቡ ተማሪዎች፤ ከጃንዋሪ 2013 ጀምሮ የቋንቋ፤ የሃይማኖ እና የግብረገብ ትምህርቶችን መማር ይጀምራሉ፡፡ መመህራንም ዝግጅታቸውን ከጃንዋሪ በፊት በማጠናቀቅ፤ የሚያስተምሩትን ትምህቶች አስቀድመው በዚህ ድረ ገጽ ላይ በሚገኘው የክፍሎች ገጽ ውስጥ ይለጥፋሉ፡፡  

የምጥን መዝገበ ቃላት ዝግጅት ተጀመረ

በትምህርት ቤቱ የሚማሩ አዳጊ ተማሪዎች ከሃይማኖታዊ ትምህርቶች በተጨማሪ የአማርኛ ቋንቋም ይማራሉ፡፡ የቋንቋ መምህራኑ፤ የልጆቹን የቃላት እውቀት ለማዳበር የሚረዳ መዝገበ ምጥን መዝገበ ቃላት ማዘጋጀት ጀምረዋል፡፡ ሁሉም የቋንቋ መምህራን፤ ለተማሪዎቻቸው የሚመጥኑ ቃላትን ማዘጋጀት ጀምረዋል፡፡

መዝገበ ቃላቱ 365 ቃላትን እንዲይዝ የታሰበ ሲሆን፤ ዓላማውም ተማሪዎች በቀን አንድ ቃል፤ በዓመት ደግሞ 365 ቃላት እንዲያውቁ ማድረግ ነው፡፡ መዝገበ ቃላቱ ሲጠናቀቅ፤ የመዝገበ ቃላቱም ይዘት (ፎርማት)ም ይሄንን ይመስላል፡፡

ምሳሌ

ቤተክርስቲያን                                                            
Betekristian....................................Picture of a Church [here]
Church

እኔ ቤተክርስቲያን መሄድ እወዳለሁ
          Ene Betekirstian Mehed Ewedalehu
I like to go to church.

ፕሮጀክቱን በሦስት ወር (ጃንዋሪ፤ፌብሩዋሪ፤ማርች) ተሰርቶ የሚጠናቀቅ ሲሆን፤ መምህርት እታፈራሁ ሰሎሞን ፕሮጀክቱን ለማስተባበር እና ለማጠናቀቅ ኃላፊነት ተቀብለዋል፡፡

Monday, December 17, 2012

የዓምደ ሃይማኖት ክፍል ወቅታዊ ሁኔታ



በናዖድ ቤተሥላሴ

የዓምደ ሃይማኖት ክፍል ተማሪዎች፤ በአንጻራዊ ደረጃም ቢሆን ለብዙ ዓመታት ሲማሩ የቆዩ፤ በዕድሜያቸውም በሰለል ያሉ ናቸው፡፡ ስለዚህ፤ ከተለመደው የትምህርት ዘዴ በተጨማሪ፤ በግል እና በቡድን የሚሰሩዋቸውን የፈጠራ እና የጥናት ፕሮጀክቶች ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም የትምህርት ዘዴ ለዓምደ ሃይማኖ ክፍል በተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ተገልጧል፡፡

ለአደጊዎቹ የሚመጥን ፕሮጀክት ለመቅረጽ ግን መጀመርያ ተማሪዎቹ ያላቸውን ፍላጎት፤ ችሎታ፤ ሙያ እና ቁሳዊ አቅም ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህንንም ለማወቅ ዲሴምበር 15 ቀን ለተገኙት ተማሪዎች ቀላል መጠይቅ እንዲሞሉ ተደርጎ ነበር፡፡ (መጠይቁን ይመልከቱ)፡፡

በዚህ ሪፖርትም በመጠይቁ የተገኙ ቁምነገሮች እንደሚከተለው በአጭሩ ቀርበዋል፡፡

Monday, December 10, 2012

የሥ.ት. ትግበራ ቅድመ ዝግጅቱ ምን ይመስላል?

በናዖድ ቤተሥላሴ

ለደብሩ አዳጊ ልጆች ትምህርት የተዘጋጀው የሥርዓተ ትምህርት (ሥ.ት) ፕሮፖዛል፤ ወደ ተግባር እንዲውል በደብሩ ኃላፋች ከተፈቀደ በኋላ፤ የአዳጊ ክፍሉ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እና ቁሳዊ ዝግጅት ጀምሯል፡፡ ቅድመ ዝግጅቱ ሦስት መልክ ያለው ነው፡፡

የሥ.ት. ትግበራው ዋና ትኩረት የመጀመርያ ሩብ ዓመት (ጃንዋሪ፤ፌብሩዋሪ፤ማርች 2013) ሥርዓተ ትምህርት ነው፡፡ ይህ የመጀመርያ ሩብ ዓመት እንደ ፓይለት ፕሮጀክት (የሙከራ ፕሮጀክት) ሆኖ፤ በሩብ ዓመቱ መጨረሻ ላይ፤ የተገኙ ስኬቶች፤ ድክመቶች እና ጉድለቶች ተገምግመው፤ አስተዳደራዊም ስትራቴጂካዊም ለውጥ ይደረጋል፡፡

በዚህም መሰረት፤ እስካሁን የተከወኑ ተግባራት እነሆ፡-

blessing

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡.......In The Name of The Father, The Son and The Holy Spirit. Amen.

Amen

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን::