
የአዳጊ
ልጆችን በማስተማር እና በማስተባበር ላይ ለሚገኙ መምህራን እና አገልጋዬች፤ የድረ-ገጽ ማኔጅመንት ሥልጠና ይሰጣል፡፡ የሥልጠናው
ዓላማ፤ መምህራን እና አስተባባሪዎች፤ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ሳምንታዊ ትምህርቶችን እና መልዕክቶችን እንዲለጥፉ ማስቻል ነው፡፡
ሥልጠናው
ሊሰጥ የታቀደው እሁድ ጃንዋሪ 24፤ 2013፤ ከሥርዓተ ቅዳሴ በኋላ ባለው ሰዓት ሲሆን፤ ሥልጠናው በጠቅላላው 4 ሰዓታት ይፈጃል፡፡
የሥልጠናውም ዋና ይዘት፤ መምህራን በዚህ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ ጽሑፍ፤ ስዕል እና ቪዲዬ የሚለጥፉበትን ቴክኒክ ማሳየት ሲሆን፤
በተዛማጅም፤ የድረ ገጹን የሚመለከቱ ጉዳዬች
ላይ ሀሳብ እና አስተያየት ይሰበሰባል፡፡
በሥልጠናው
ወቅት፤ እያንዳንዱ ሰልጣኝ፤ የራሱን ላፕቶፕ ኮምፒውተር የሚጠቀም ሲሆን፤ የስልጠናው አዘጋጆችም ለሰልጣኞች የተዘጋጁ የሥልጠና ወረቀቶችን
ይሰጣሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፤ እያንዳንዱ ሠልጣኝ፤ የተዘጋጁ ትምህርታዊ ጽሑፎችን በድረ ገጾች ላይ በመለጠፍ፤ ተግባራዊ ልምምድ ያደርጋል፡፡
ይህ
ሥልጠና፤ የአዳጊ ልጆች መምህራንን ቴክኒካዊ ብቃት ለመጨመር ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ ሲሆን፤ በቀጣይም ሌሎች የቡድን እና የግል
ሥልጠናዎች ይደረጋሉ፡፡
No comments:
Post a Comment
እናመሰግናለን፡፡ተሳትፎዎን ይቀጥሉ፡፡