Sunday, May 11, 2014

የልጆች መምህር ፍለጋ

የደብራችን የአዳጊ ልጆች ትምህርት ክፍል፤ የአማርኛ ፊደል ያጠናቀቁ ተማሪዎችን የአማርኛ ቃላት ግንባታ እና ንባብ የሚያስተምር መምህር ይፈልጋል፡፡ ለማስተማር እችላለሁ የሚል መምህር ወይም መምህራን የሚከተሉትን ነጥቦች ያካተተ መረጃ እንዲልኩልን እንጠይቃለን፡፡

ትምህርትቤቱ መምህር የሚፈልገው ለአንድ ክፍል ተማሪዎች ሲሆን ተማሪዎቹ የተማሪዎቹ በዛት 25 ይደርሳል፡፡ ክፍሉ በቂ መቀመጫዎች እና ኋይት ቦርድ አለው፡፡ በተጨማሪም ትምህርትቤቱ ሌሲዲ ፕሮጀክተር እና ኦቨር ሄድ ፕሮጀክተር ማቅረብ ይችላል፡፡ የአማርኛ ክፍለ ጊዜ የሚጀምረው ልጆቹ ከቁርባን ከተመለሱ በኋላ ማለትም 10 ኤ.ሜ የሚጀምር ሲሆን የሚያልቀው ደግሞ 11 ሰዓት ነው፡፡
የማመልከቻ ይዘት
·         ሙሉ ስም
·         ስልክ ወይም ኢ-ሜይል
·         የሚያስተምሩበትን ዋጋ መጠን
·         የሚያስተምሩበትን ዓመታዊ ካሪኩለም ወይም ቴክስት ቡክ
·         በዓመቱ መጨረሻ ተማሪዎቹ እንዲህ እንዲያደርጉ ወይም ይሄ ችሎታ እንዲኖራቸው አደርጋለሁ የሚል የግብ መግለጫ
·         ስኬታማ ለመሆን ከትምህርትቤቱ የሚፈልጉትን ድጋፍ ዝርዝር

አመልካቾች ከላይ ያሉትን ነጥቦችን ያካተተ ማመልከቻ (ፕሮፖዛል) በማዘጋጀት በኢ-ሜይል dmk12@comcast.net naodforkids@gmail.com መላክ ይችላሉ፡፡
 
አመልካቾች የሚያቀርቡትን ፕሮፖዛል ለቤተክርስቲያኑ አስተዳደር ቀርቦ ተቀባይነት ካላገኘ ቅጥር አይካሄድም፡፡

 

Sunday, May 4, 2014

አዲስ የትምህርት መጀመርያ ሰዓት


ማሳሰቢያ

 የአዳጊ ልጆች ትምህርት የሚጀመረው ከቁርባን በኋላ ነበር፡፡ አሁን ግን ልጆች ስለ ቁርባን ሥርዓት እና ስለ ሃይማኖታቸው በደንብ እንዲማሩ ለማድረግ ትምህርት የሚጀመርበትን ሰዓት ከቁርባን ሰዓት በፊት ከ8፡00 ጀምሮ አድርገነዋል፡፡ ስለዚህ ከሚቀጥለው ሳምንት እሁድ ጀምሮ፡-

1ኛ. ልጆች ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ፤ በቀጥታ ወደ መማርያ ክፍላቸው ይገባሉ፡፡ የተመደቡ ካህናት እና ዘማርያንም የሃይማኖት እና ሥርዓት ትምህርት ያስተምራሉ፡፡

2ኛ. የቁርባን ሰዓት ሲደርስ፤ ተማሪዎች ተሰልፈው ወደ ስርዓተ ቁርባን ይሄዳሉ

3ኛ. ከቁርባን በኋላ ተመልሰው ወደ መማርያ ክፍላቸው ይገቡና ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ፡፡

ይህ አዲስ የትምህርት ልጆች በሥርዓተ ቁርባን ጊዜ የሚፈጽሙትን ስህተት ለማስተካከል እና ተጨማሪ የሃይማኖት ትምህርት እንዲያገኙ ለማድረግ ነው፡፡

የአዳጊዎች ክፍል የትምህርት ክፍል

Sunday, March 9, 2014

ረቂቅ የውስጥ አደረጃጀት እና አስተዳደር መመሪያ (by-law)

ለአስተያየት የቀረበ

 

የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን

የአዳጊዎች ትምህርት ክፍል

የውስጥ አደረጃጀት እና አስተዳደር መመሪያ (by-law)

(ረቂቅ)

03/09/2014

 የመዋቅሩን  ቻርት ለማየት የይህን የይጫኑ

1.   ዋና አስተባባሪ…….

·        የአዳጊ ልጆች ትምህርት እንቅስቃሴ ሁሉ ተጠሪ ነው

·        ለደብሩ አስተዳደር ዓመታዊ የበጀት ጥያቄ ያቀርባል

·        ለደብሩ አስተዳደር የሩብ ዓመት የሥራ ክንውን ሪፖርት ያቀርባል

·        የክፍል አስተባባሪዎችን በመደበኛ ስብሰባ ይሰበስባል፤ ያስተባብራል

·        አስቸኳይ ስብሰባዎችን ይጠራል

·        ሰነዶችን ላይ ይፈርማል

 

2.  ረዳት አስተባባሪ……..

·        በመዋቅሩ እንደተመለከተው፤ የወላጆች፤ የመምህራን እና የትምህርት ዝግጅት ክፍሎች የበላይ ተጠሪ ነው

·        የዓምደ ሃይማኖት ተማሪዎችን ያስተምራል

·        ለትምህርትቤቱ ማጠናከሪያ እና ገቢ ማግኛ ፕሮጀክቶችን ይነድፋል

·        ካህናት ተማሪዎችን በየቀኑ እንዲባርኩ እና እንዲመክሩ ይጋብዛል

·        ዋና አስተባባሪ የሚወክለውን ሥራ ሁሉ ይሰራል

 

3.  ፀሐፊ……

·        በመዋቅሩ እንደተመለከተው፤ የቱተር፤ የቴክኖሎጂ፤ የጥናት እና ሥልጠና፤ የምርት እና ፕሮጀክት አስተባባሪዎች የበላይ ተጠሪ ነው

·        የትምህርትቤቱን ሰነዶች ሁሉ ዶክመንት ያደርጋል

·        የተማሪዎች እና የወላጆችን ምዝገባ ያካሂዳል

·        ትምህርትቤቱ ከወላጆች እና ከአስተዳደር ጋር የሚያደርገውን የደብዳቤ ልውውጥ ዶክመንት ያደርጋል

·        ስለ ትምህርትቤቱ ሙሉ አና ወቅታዊ መረጃ የሚሰጥ ጽሑፍ በብሮሸር ያዘጋጃል፤ በድረ ገጽ ላይ ይለጥፋል፤ በኢሜል እና ፖስታ ይልካል

·        ከክፍሎች የሚመጡ የሩብ ዓመት እና የዓመት በበጀት ጥያቄዎችን፤ የሥራ ሪፖርቶችን ያቀናብራል

 

4.  የወላጆች አስተባባሪ

·        የወላጆችን ሙሉ መረጃ ይይዛል

·        የወላጅ አገልጋዮች መተዳደሪያ ደንብ ያዘጋጃል

·        ወላጆች በየክፍሉ እንዲያገለግሉ ያበረታታል፤ ይቀሰቅሳል

·        ለፈቃደኛ ወላጆች ፕሮግራም ያወጣል፤ ይከታተላል

·        ወላጆችን ስለ ልጆቻቸው ጉዳይ ያነጋግራል

·        መምህራንን ለሚያስቸግሩ ልጆች የምክር አገልግሎት እንዲሰጥ ያደርጋል

·        ወላጆችን ሰብስቦ ያወያያል፤ አስተያየት ይቀበላል

·        የልጆች በዓላትን እና ዝግጅቶችን ያስተባብራል

·        ለትምህርትቤቱ ማጠናከሪያ ገቢ ያሰባስባል

·        የሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ እና የበጀት ጥያቄ ያቀርባል

·        የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል

 

5.  የመምህራን አስተባባሪ)

·        የመምህራን መተዳደሪያ ደንብ ያዘጋጃል

·        የመምህራንን ሙሉ መረጃ መዝግሞ ይይዛል

·        በጎ ፈቃድ መምህራንን ይመለምላል፤ ይደለድላል

·        የተማሪዎችን ዓመታዊ ውጤት እና ሰርተፊኬት ያጠናቅራል

·        ለመምህራን የሙያ ማጎልበቻ ሥልጠና ያዘጋጃል

·        የመምህራን ውይይት ፕሮግራም ያዘጋጃል

·        የመምህራን እና ወላጆች የውይይት መርሀግብርን ከወላጆች አስተባባሪ ጋር በመሆን ያዘጋጃል

·        የሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ እና የበጀት ጥያቄ ያቀርባል

·        የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል

 

 

6.  የትምህርት ዝግጅት አስተባባሪ

·        ያለው ካሪኩለም ተገምግሞ እንዲሻሻል ያደርጋል

·        ለሚሰጡት ትምህርቶች ሁሉ መርጃ መጽሐፍትን ያዘጋጃል፤ ይገዛል፤ ያሰባስባል

·        የቤተመጽሐፍት አገልግሎትን ያጠናክራል

·        የሩብ ዓመት ዜና መጽሔት ዝግጅትን ይመራል

·        የህትመት እና ኮፒ አገልግሎቶችን ይሰጣል

·        የሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ እና የበጀት ጥያቄ ያቀርባል

·        የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል

 

7.  የምርት እና ፕሮጀክት አስተባባሪ

·        የማስተማርያ መርጃ ቁሳቁሶችን ያመርታል፤ ይገዛል፤ ያቀርባል

·        የክፍሎችን እና የማስተማርያ ቁሳቁሶችን እድሳት እና ጥገና ያደርጋል

·        የትምህርት ቤት ግንባታ እንዲጀመር ቅስቀሳ፤ ትምህርት እና የምክክር ፕሮግራም ያዘጋጃል

·        የሩብ ዓመት በጀት ያቀርባል

·        የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል

 

8.  የቱተር አገልጎት አስተባባሪ

·        የተማሪዎችን የቀለም ትምህርት ደረጃ እና መረጃ ይሰበስባል

·        የቱተር ፕሮግራም መተዳደሪያ ደንብ ያዘጋጃል

·        ለውጤታማ ተማሪዎች የአርአያነት ሽልማት ይሰጣል

·        ከምዕመናን ውስጥ የቱተር አገልግሎት መስጠት የሚፈልጉ ባለሙያዎችን ይመለምላል

·        የሰመር ፕሮግራሞችን ከወላጆች አስተባባሪ ጋር በመተባባር ያዘጋጃል

·        የሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ እና የበጀት ጥያቄ ያቀርባል

·        የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል

 

9.  የቴክኖሎጂ አገልግሎት አስተባባሪ

·        ከደብሩ የአይ.ቲ. ቲም ጋር በጋራ ይሰራል

·        የአይ. ቲ. ባለሙያ ወላጆን ያሰባስባል፤ ያስተባብራል

·        የአዳጊዎች ክፍልን ድረ ገጽ ያስተዳድራል

·        ለመምህራን እና ወላጆች ድረ ገጹን ያስተዋውቃል፤  

·        ተማሪዎች ድረ ገጽ ላይ ትምህርቶች እና የቤት ሥራ በወቅቱ እንዲለጠፍላቸው ያደርጋል

·        የተማሪ እና ወላጆች የምዝገባ እና ትምህርት መረጃዎች በኮምፒውተር ዳታ ቤዝ እንዲቀመጡ ያደርጋል

·        የሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ እና የበጀት ጥያቄ ያቀርባል

·        የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል

 

10.የጥናት እና ሥልጠና አስተባባሪ

·        በትምህርት ቤቱ እንቅስቃሴ፤ ስኬት እና ድክመት ላይ ጥናቶችን ያደርጋል

·        የጥናት ውጤቶችን ለሚመለከታቸው ክፍሎች ያሳውቃል

·        የሌሎች መንፈሳዊ ትምህርትቤቶችን ልምድ እያጠና ያካፍላል

·        የመምህራን ብቃት ለመጨመር፤ ወላጆችን ፍላጎት ለማሳደግ የሚረዱ ተጨማሪ የኮምፒውተርም ሆነ ሌሎች የሙያ ሥልጠናዎችን ያስተባብራል፤ ያዘጋጃል

·         የሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ እና የበጀት ጥያቄ ያቀርባል

·        የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል

 

 

Thursday, February 27, 2014

ከአንድ-ለሁሉም ወደ አንድ-ለአራት (የፊደል ቤት ተማሪዎች አዲስ የክፍል ሥርዓት)




የፊደል ቤት ተማሪዎች በአብዛኛው እድሜያቸው ከ5-7 የሚደርሱ ልጆች ሲሆኑ፤ በክፍል ውስጥም የሚማሩት ፊደል መቁጠር እና መጻፍ መለማመድ ነው፡፡ በሃይማኖትም ክፍለ ጊዜ ቀላል መዝሙሮችን ያጠናሉ፤ የቤተክርስቲያን ስዕላትን መለየት ይማራሉ፡፡ የተማሪዎቹ ቁጥር 20ም ይሁን 30፤ ትምህርቱ የሚሰጣቸው በአንድ መምህር ነበር (አንድ-ለሁሉም)፡፡


የአንድ-ለሁሉም የትምህርት አሰጣጥ ጠቃሚ የሚሆንበት ሁኔታዎች ቢኖሩም፤ የወላጆችን በትምህርት አሰጣጥ ውስጥ በብዛት ለማሳተፍ፤ ተማሪዎችንም በቅርብ ለመከታተል በቂ መድረክ አይሰጥም፡፡ በሁለተኛውም የመምህራን እና የወላጆች ጉባዔም ወቅት እንደተገለጸው፤ ከፌብሩዋሪ 2014 ጀምሮ የጀማሪ ክፍል የትምህርተ አሰጣጥ አንድ-ለአራት እንዲሆን ተደርጓል፡፡


የአንድ-ለአራት የትምህርት አሰጣጥ በአጭሩ፡- አንድ መምህር በክብ ጠረጴዛ ላይ በአማካይ 4 ተማሪዎችን ያስተምራል፡፡ በክፍል ውስጥ 28 ተማሪዎች ቢኖሩ፤ 7 ክብ ጠረጴዛዎች ይኖራሉ፤ 7 መምህራንም ይኖራሉ፡፡ ተማሪዎቹን የሚደለድሉት መምህራኑ ሲሆኑ፤ በየጠረጴዛው በመምህርነት የሚመደቡ ደግሞ የልጆች ወላጆች ናቸው፡፡ የዕለቱ ትምህርት የሚዘጋጀው እና የሚባዛው በመደበኛ የክፍሉ መምህራን ነው፡፡

በዚህ መሰረት፤ በአሁኑ ሰዓት ያለው የተማሪዎች ምደባ እና የወላጅ መምህራን ዝርዝር ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ተመልክቷል፡፡ ይህ ዝርዝር፤ በመምህራኑ እና በወላጅ መምህራን ግምገማ መሰረት በየወቅቱ ሊለወጥ ይችላል፡፡
 
ዋና መምህራን

1.      ሐና ደጋ…ፊደል አስተማሪ

2.     ሰሎሞን ኪዳኔ…..ግብረ ገብ አስተማሪ
 

 
ምድብ
የተማሪ ሥም
ወላጅ መምህራን
 
1
አብኬም በረከት 
ቤተልሄም ተመስገን
ሊያ ቢንያም
ኤደን ፈለቀ
ሰብለ/ሕይወት
 
 
2
ህዝቅኤል ሰለሞን
ማራኪ ግዛው
አቢጌል ታሪኩ
ፌቨን እስክንድር
ቤዛ/ኢየሩ
 
3
በረከት ዋለልኝ
ፍቅር ሠይፈ
ቤተል አይምሮ
አቤኔዘር ታዬ
ዓብይ/ገነት
 
4
ኤልዳ ሙሉጌታ
ኤደን መሰረት
ፀጋ ታፈሰ
ሄይመን አሌክስ
ሶፍያ/አልማዝ
 
5
ልደት አርጋው
ሃና አክሊል
ሊዲያ መስፍን
ሜሪ ሰለሞን
መሰረት
 
6
ሙሴ ተድላ
ረድኤት መስፍን
ረድኤት ዋለልኝ
ሶሊያና ሙሉጌታ
ሙላት
 
7
ናቲ አትክልቲ
ያሬድ ስንታየሁ
ካሌብ መሳፍንት
መፍትሄ ዳንኤል
ማቲ ኩዊን
አማኑኤል ተመስገን
ቤተልሔም አሰፋ
መለይ ፈቃደ
 
(ትልቅ ክብ ጠረጴዛ ላይ ያሉ)
8
ኖላዊ ግዛው
ኪሩቤል መስፍን
ዳዊት ፈለቀ
ናሆም መስፍን
ሐረገወይን
 

blessing

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡.......In The Name of The Father, The Son and The Holy Spirit. Amen.

Amen

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን::