Sunday, May 12, 2013

ለተማሪዎች አዲስ የክፍል ድልድል የማድረግ ዕቅድ

ለወላጆች የተላከ ማሳሰቢያ ደብዳቤ፡

በደብራችን የአዳጊዎች ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩ 150 መደበኛ እና ከ50 በላይ ኢ-መደበኛ ተማሪዎች አሉ፡፡ ሁሉም ተማሪዎች የሚማሩበት ተመጣጣኝ ዓመታዊ ሥርዓተ ትምህርት እና 15 በጎ ፈቃደኛ አስተማሪዎች አላቸው፡፡ አዳጊዎቹ በመሰረታዊነት የሚማሩትም አማርኛ ቋንቋ፤ ሃይማኖት እና ግብረ ገብ ነው፡፡

በየሩብ ዓመቱም፤ የተማሪዎቹን የመማር ደረጃ የሚለካ እና የመምህራኑን የማስተማር ዘዴ ውጤታማነት የሚለካ ፈተና ይሰጣል፡፡ የመጀመርያው ሩብ ዓመት ፈተናም ማርች 31 2013 ተሰጥጧል፡፡

የዚህ ሩብ ዓመት የተማሪዎች የፈተና ውጤት በግልጽ እንደሚያሳየው ከሆነ፤ ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች ለተመደቡበት ክፍል የሚመጥን ደረጃ ላይ አይደሉም፡፡ ውጤታቸው፤ አብረዋቸው ከሚማሩ ሌሎች ተማሪዎች አንጻር ሲታይ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ወይም እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡

የልጅዎን ደረጃ ለማወቅ፤ እባክዎ፤ የልጅዎ ውጤት ሪፖርት ካርድ ጀርባ ላይ ያሉትን መረጃዎች ያንብቡ፡፡

የትምህርት አስተዳደሩም፤ የችግሩን ምክንያት በዝርዝር ለማየት ሞክሯል፡፡ ለችግሩ ምክንያት ከሆኑት መካከል ዋነኛው የወላጆች ክትትል እና ድጋፍ ማነስ ሲሆን፤ የመምህራን እጥረትም ሌላው ችግር ነው፡፡ ሌላው ቁልፍ ችግር ግን፤ ጥቂት የማይባሉ ልጆች፤ አሁን ለሚማሩበት ክፍል በዕድሜ ወይም በዕውቀት ደረጃ የማይመጥኑ መሆናቸው ነው፡፡

ስለዚህ፤ ተማሪዎች በቀጣዩ ሩብ ዓመት (ኤፕሪል እስከ ጁን) ውስጥ በሚያሳዩት መሻሻል መሰረት፤ ወደ አዲስ እና የሚመጥናቸው ክፍል ይደለደላሉ፡፡ የዚህ ማሳሰቢያም ዓላማ፤ ወላጆች ለደብራችን ትምህርት ቤት ጥራት እና ውጤታማነት ለምናደርገው ጥረት በጎ ድጋፋቸውን እና አስተያየታቸውን ከመስጠት በተጨማሪ፤ ተማሪ ልጆቻቸው የሚሰጣቸውን የክፍል ሥራ እና የቤት ሥራ በማሰራት እንዲረዱን ለማሳወቅ ነው፡፡

የአዳጊዎች ትምህርት ክፍል






No comments:

Post a Comment

እናመሰግናለን፡፡ተሳትፎዎን ይቀጥሉ፡፡

blessing

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡.......In The Name of The Father, The Son and The Holy Spirit. Amen.

Amen

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን::