Sunday, February 24, 2013

ለመምህራን የድረ ገጽ ማኔጅመንት ሥልጠና ተሰጠ

የአዳጊ ልጆች መምህራን በዛሬው ዕለት የድረ ገጽ ማኔጅመንት ሥልጠና ወስደዋል፡፡ ሥልጠናው የተዘጋጀው ‹‹ልጆቻችንን የሚገለግሉትን መምህራን እናገልግላቸው›› በሚል መርህ ሲሆን፤ በሥልጠናው ወቅት መምህራን ራሳቸውን ችለው፤ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ጽሑፍ፤ ስዕል እና ቪዲዬ ማውጣት የሚችሉበትን ዘዴዎች ተምረዋል፤ ተለማምደዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በሚለጥፉት ትምህርቶች ውስጥ ደጋፊ የውስጥና የውጪ ሊንኮችን መፍጠር የሚችሉበትን መንገድ አይተዋል፡፡

ከግራ ወደ ቀኝ፡- ቢኒያም ዮሴፍ፤ ዳንኤል ኃይለመስቀል፤ ሰሎሞን ወርቁ፤ መኮንን አክሌ፤ ሐና ደጋ
ለሠልጣኞቹ የተሰጡ ሁለት መማርያ ወረቀቶች ነበሩ፡፡ 1ኛ፡-ለሥልጠናው ዕለት ተዘጋጅተው መምጣት ያለባቸውን ጉዳዬች የሚያብራራ ወረቀት ሲሆን  ሁለተኛው ደግሞ በስድስት ክፍለ ትምህርቶች የተከፋፈለ የትምህርት ወረቀት ነው፡፡ የትምህርት ወረቀቱን ለማየት ይህንን ይጫኑ፡፡

ይህንን የድረ ገጽ ማኔጅመንት ሞያ የቀሰሙት መምህራን፤ በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ፤ በየክፍላቸው የሚያስተምሩትን ትምህርቶች፤ በዚህ ድረ ገጽ ዓምዶች ላይ መለጠፍ ይጀምራሉ፡፡  

ይሄ ሥልጠና፤ ለመምህራን ከሚሰጡ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናዎች አንዱ ሲሆን፤ ወደፊት በዚህ ስልጠና ላልተሳተፉ መምህራን እና አገልጋዬች፤ ሌሎች ተዛማጅ የኮምፒውተር እና የሥርዓተ ትምህርት አተገባበር ሥልጠናዎች ይሰጣሉ፡፡

Thursday, February 21, 2013

ማስታወቂያ

ባለፈው ሳምንት የንባብ ክፍል ተማሪዎች ከመደበኛዉ ስርኣተ ትምህርቱ ያላገኙትን ለማካካስ እንዲመች ተማሪዎች እስካሁን ያሉትን መልመጃዎች እንዲጨርሱ ወላጆች ይረዷችዉ ዘንድ በኣክብሮት እንጠይቃለን።
 
ከንባብ ክፍል

Thursday, February 14, 2013

የድረ-ገጽ ማኔጅመንት ሥልጠና ይሰጣል



የአዳጊ ልጆችን በማስተማር እና በማስተባበር ላይ ለሚገኙ መምህራን እና አገልጋዬች፤ የድረ-ገጽ ማኔጅመንት ሥልጠና ይሰጣል፡፡ የሥልጠናው ዓላማ፤ መምህራን እና አስተባባሪዎች፤ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ሳምንታዊ ትምህርቶችን እና መልዕክቶችን እንዲለጥፉ ማስቻል ነው፡፡
ሥልጠናው ሊሰጥ የታቀደው እሁድ ጃንዋሪ 24፤ 2013፤ ከሥርዓተ ቅዳሴ በኋላ ባለው ሰዓት ሲሆን፤ ሥልጠናው በጠቅላላው 4 ሰዓታት ይፈጃል፡፡ የሥልጠናውም ዋና ይዘት፤ መምህራን በዚህ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ ጽሑፍ፤ ስዕል እና ቪዲዬ የሚለጥፉበትን ቴክኒክ ማሳየት ሲሆን፤ በተዛማጅም፤  የድረ ገጹን የሚመለከቱ ጉዳዬች ላይ ሀሳብ እና አስተያየት ይሰበሰባል፡፡
በሥልጠናው ወቅት፤ እያንዳንዱ ሰልጣኝ፤ የራሱን ላፕቶፕ ኮምፒውተር የሚጠቀም ሲሆን፤ የስልጠናው አዘጋጆችም ለሰልጣኞች የተዘጋጁ የሥልጠና ወረቀቶችን ይሰጣሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፤ እያንዳንዱ ሠልጣኝ፤ የተዘጋጁ ትምህርታዊ ጽሑፎችን በድረ ገጾች ላይ በመለጠፍ፤ ተግባራዊ ልምምድ ያደርጋል፡፡
ይህ ሥልጠና፤ የአዳጊ ልጆች መምህራንን ቴክኒካዊ ብቃት ለመጨመር ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ ሲሆን፤ በቀጣይም ሌሎች የቡድን እና የግል ሥልጠናዎች ይደረጋሉ፡፡

blessing

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡.......In The Name of The Father, The Son and The Holy Spirit. Amen.

Amen

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን::