የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
የአዳጊዎች ትምህርት ክፍል
የውስጥ አደረጃጀት እና አስተዳደር መመሪያ (by-law)
(ረቂቅ)
03/09/2014
1.
ዋና አስተባባሪ…….
·
የአዳጊ ልጆች ትምህርት እንቅስቃሴ ሁሉ ተጠሪ ነው
·
ለደብሩ አስተዳደር ዓመታዊ የበጀት ጥያቄ ያቀርባል
·
ለደብሩ አስተዳደር የሩብ ዓመት የሥራ ክንውን ሪፖርት ያቀርባል
·
የክፍል አስተባባሪዎችን በመደበኛ ስብሰባ ይሰበስባል፤ ያስተባብራል
·
አስቸኳይ
ስብሰባዎችን ይጠራል
·
ሰነዶችን
ላይ ይፈርማል
2.
ረዳት አስተባባሪ……..
·
በመዋቅሩ እንደተመለከተው፤ የወላጆች፤ የመምህራን እና የትምህርት ዝግጅት ክፍሎች የበላይ ተጠሪ ነው
·
የዓምደ ሃይማኖት ተማሪዎችን ያስተምራል
·
ለትምህርትቤቱ ማጠናከሪያ እና ገቢ ማግኛ ፕሮጀክቶችን ይነድፋል
·
ካህናት ተማሪዎችን በየቀኑ እንዲባርኩ እና እንዲመክሩ ይጋብዛል
·
ዋና አስተባባሪ የሚወክለውን ሥራ ሁሉ ይሰራል
3.
ፀሐፊ……
·
በመዋቅሩ እንደተመለከተው፤ የቱተር፤ የቴክኖሎጂ፤ የጥናት እና ሥልጠና፤ የምርት እና ፕሮጀክት አስተባባሪዎች
የበላይ ተጠሪ ነው
·
የትምህርትቤቱን ሰነዶች ሁሉ ዶክመንት ያደርጋል
·
የተማሪዎች እና የወላጆችን ምዝገባ ያካሂዳል
·
ትምህርትቤቱ ከወላጆች እና ከአስተዳደር ጋር የሚያደርገውን የደብዳቤ ልውውጥ ዶክመንት ያደርጋል
·
ስለ ትምህርትቤቱ ሙሉ አና ወቅታዊ መረጃ የሚሰጥ ጽሑፍ በብሮሸር ያዘጋጃል፤ በድረ ገጽ ላይ ይለጥፋል፤
በኢሜል እና ፖስታ ይልካል
·
ከክፍሎች የሚመጡ የሩብ ዓመት እና የዓመት በበጀት ጥያቄዎችን፤ የሥራ ሪፖርቶችን ያቀናብራል
4.
የወላጆች አስተባባሪ
·
የወላጆችን ሙሉ መረጃ ይይዛል
·
የወላጅ አገልጋዮች መተዳደሪያ ደንብ ያዘጋጃል
·
ወላጆች በየክፍሉ እንዲያገለግሉ ያበረታታል፤ ይቀሰቅሳል
·
ለፈቃደኛ ወላጆች ፕሮግራም ያወጣል፤ ይከታተላል
·
ወላጆችን ስለ ልጆቻቸው ጉዳይ ያነጋግራል
·
መምህራንን ለሚያስቸግሩ ልጆች የምክር አገልግሎት እንዲሰጥ ያደርጋል
·
ወላጆችን ሰብስቦ ያወያያል፤ አስተያየት ይቀበላል
·
የልጆች በዓላትን እና ዝግጅቶችን ያስተባብራል
·
ለትምህርትቤቱ ማጠናከሪያ ገቢ ያሰባስባል
·
የሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ እና የበጀት ጥያቄ ያቀርባል
·
የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል
5.
የመምህራን አስተባባሪ)
·
የመምህራን መተዳደሪያ ደንብ ያዘጋጃል
·
የመምህራንን ሙሉ መረጃ መዝግሞ ይይዛል
·
በጎ ፈቃድ መምህራንን ይመለምላል፤ ይደለድላል
·
የተማሪዎችን ዓመታዊ ውጤት እና ሰርተፊኬት ያጠናቅራል
·
ለመምህራን የሙያ ማጎልበቻ ሥልጠና ያዘጋጃል
·
የመምህራን ውይይት ፕሮግራም ያዘጋጃል
·
የመምህራን እና ወላጆች የውይይት መርሀግብርን ከወላጆች አስተባባሪ ጋር በመሆን ያዘጋጃል
·
የሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ እና የበጀት ጥያቄ ያቀርባል
·
የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል
6.
የትምህርት ዝግጅት አስተባባሪ
·
ያለው ካሪኩለም ተገምግሞ እንዲሻሻል ያደርጋል
·
ለሚሰጡት ትምህርቶች ሁሉ መርጃ መጽሐፍትን ያዘጋጃል፤ ይገዛል፤ ያሰባስባል
·
የቤተመጽሐፍት አገልግሎትን ያጠናክራል
·
የሩብ ዓመት ዜና መጽሔት ዝግጅትን ይመራል
·
የህትመት እና ኮፒ አገልግሎቶችን ይሰጣል
·
የሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ እና የበጀት ጥያቄ ያቀርባል
·
የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል
7.
የምርት እና ፕሮጀክት አስተባባሪ
·
የማስተማርያ መርጃ ቁሳቁሶችን ያመርታል፤ ይገዛል፤ ያቀርባል
·
የክፍሎችን እና የማስተማርያ ቁሳቁሶችን እድሳት እና ጥገና ያደርጋል
·
የትምህርት ቤት ግንባታ እንዲጀመር ቅስቀሳ፤ ትምህርት እና የምክክር ፕሮግራም ያዘጋጃል
·
የሩብ ዓመት በጀት ያቀርባል
·
የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል
8.
የቱተር አገልጎት አስተባባሪ
·
የተማሪዎችን የቀለም ትምህርት ደረጃ እና መረጃ ይሰበስባል
·
የቱተር ፕሮግራም መተዳደሪያ ደንብ ያዘጋጃል
·
ለውጤታማ ተማሪዎች የአርአያነት ሽልማት ይሰጣል
·
ከምዕመናን ውስጥ የቱተር አገልግሎት መስጠት የሚፈልጉ ባለሙያዎችን ይመለምላል
·
የሰመር ፕሮግራሞችን ከወላጆች አስተባባሪ ጋር በመተባባር ያዘጋጃል
·
የሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ እና የበጀት ጥያቄ ያቀርባል
·
የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል
9.
የቴክኖሎጂ አገልግሎት አስተባባሪ
·
ከደብሩ የአይ.ቲ. ቲም ጋር በጋራ ይሰራል
·
የአይ. ቲ. ባለሙያ ወላጆን ያሰባስባል፤ ያስተባብራል
·
የአዳጊዎች ክፍልን ድረ ገጽ ያስተዳድራል
·
ለመምህራን እና ወላጆች ድረ ገጹን ያስተዋውቃል፤
·
ተማሪዎች ድረ ገጽ ላይ ትምህርቶች እና የቤት ሥራ በወቅቱ እንዲለጠፍላቸው ያደርጋል
·
የተማሪ እና ወላጆች የምዝገባ እና ትምህርት መረጃዎች በኮምፒውተር ዳታ ቤዝ እንዲቀመጡ ያደርጋል
·
የሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ እና የበጀት ጥያቄ ያቀርባል
·
የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል
10.የጥናት እና ሥልጠና አስተባባሪ
·
በትምህርት ቤቱ እንቅስቃሴ፤ ስኬት እና ድክመት ላይ ጥናቶችን ያደርጋል
·
የጥናት ውጤቶችን ለሚመለከታቸው ክፍሎች ያሳውቃል
·
የሌሎች መንፈሳዊ ትምህርትቤቶችን ልምድ እያጠና ያካፍላል
·
የመምህራን ብቃት ለመጨመር፤ ወላጆችን ፍላጎት ለማሳደግ የሚረዱ ተጨማሪ የኮምፒውተርም ሆነ ሌሎች
የሙያ ሥልጠናዎችን ያስተባብራል፤ ያዘጋጃል
·
የሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ እና የበጀት
ጥያቄ ያቀርባል
·
የሩብ ዓመት የክንውን ሪፖርት ያቀርባል