ኖቬምበር
3 2013 በተጠራው የወላጆች እና መምህራንን የምክክር ስብሰባ ላይ 41 ወላጆች እና መምህራን እንዲሁም የደብሩ አስተዳደር ተገኝተው
ነበር፡፡ በዕለቱ በአዳጊዎች ትምህርት ቤቱ እንቅስቃሴዎች፤ ጥንካሬዎች እና ድክመቶች ውይይት ተደርጓል፡፡
ከውይይቱ በተጨማሪ ግን
ወላጆች ስማቸውን ሳይገልጹ እንዲመልሱት የተዘጋጀ መጠይቅ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ መጠይቁ 17 ጥያቄዎች ያሉት ሲሆን የጥያቄዎቹም ይዘት
በተማሪ ልጆች፤ በመምህራን፤ በወላጆች ጥረት፤ በትምህርት ቤቱ የወደፊት ተስፋ፤ እና የገንዘብ ክፍያን ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ነበሩ፡፡
(የታደለውን መጠይቅ ለማየት ይህንን ይጫኑ)
ወላጆች
በመጠይቁ ወረቀት ላይ ያሰፈሩት መልሶች ሲጠቃለሉ በአብዛኛው በጎ እና ደጋፊ አመለካከት እንዳላቸው ሲያመለክት፤ አሉታዊ መልስ የሰጡባቸው
ጥያቄዎች ለወደፊቱ በትምህርት ቤቱ ጥራት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ የሚረዱ ጥቆማዎች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ (የተጠናቀረውን የወላጆችመልስ እና ውጤት ለማየት ይህንን ይጫኑ)፡፡ ውጤቱም
ለወላጆች በቤት አድራሻቸው ተልኳል፡፡
No comments:
Post a Comment
እናመሰግናለን፡፡ተሳትፎዎን ይቀጥሉ፡፡