Thursday, December 5, 2013

ወላጆች ስለ ትምህርትቤታችን ምን ይላሉ?

ኖቬምበር 3 2013 በተጠራው የወላጆች እና መምህራንን የምክክር ስብሰባ ላይ 41 ወላጆች እና መምህራን እንዲሁም የደብሩ አስተዳደር ተገኝተው ነበር፡፡ በዕለቱ በአዳጊዎች ትምህርት ቤቱ እንቅስቃሴዎች፤ ጥንካሬዎች እና ድክመቶች ውይይት ተደርጓል፡፡

ከውይይቱ በተጨማሪ ግን ወላጆች ስማቸውን ሳይገልጹ እንዲመልሱት የተዘጋጀ መጠይቅ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ መጠይቁ 17 ጥያቄዎች ያሉት ሲሆን የጥያቄዎቹም ይዘት በተማሪ ልጆች፤ በመምህራን፤ በወላጆች ጥረት፤ በትምህርት ቤቱ የወደፊት ተስፋ፤ እና የገንዘብ ክፍያን ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ነበሩ፡፡ (የታደለውን መጠይቅ ለማየት ይህንን ይጫኑ)

ወላጆች በመጠይቁ ወረቀት ላይ ያሰፈሩት መልሶች ሲጠቃለሉ በአብዛኛው በጎ እና ደጋፊ አመለካከት እንዳላቸው ሲያመለክት፤ አሉታዊ መልስ የሰጡባቸው ጥያቄዎች ለወደፊቱ በትምህርት ቤቱ ጥራት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ የሚረዱ ጥቆማዎች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ (የተጠናቀረውን የወላጆችመልስ እና ውጤት ለማየት ይህንን ይጫኑ)፡፡  ውጤቱም ለወላጆች በቤት አድራሻቸው ተልኳል፡፡

Sunday, December 1, 2013

የልምድ ልውውጥ ሪፖርት

በናዖድ ቤተሥላሴ
በደብራችን በደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (3010 Earl Pl NE Washington, DC 20018) የሚገኘውንም የአዳጊዎች ትምህርት ክፍል ለማጠናከር እየተደረጉ ካሉ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አንዱ የሌሎች እህት አብያተ ክርስቲያናትን ልምድ እና አሰራር ልምድ መቅሰም ነው፡፡
 
እሁድ ዲሴምበር 02 2013 በደብረ ገነት መድኃኒአለም ቤተክርስቲያን (4401 Old Branch Avenue  Temple Hills, MD 20748) ተገኝቼ፤ የአዳጊ ልጆች እና ወጣቶች ትምህርት አሰጣጥን ለመጎብኘት፤ ከልምዳቸውም ብዙ ለመማር ችያለሁ፡፡ ያገኘሁትንም መሰረታዊ ትምህርት፤ ጠቃሚ ልምድ እና ምክር በአጭሩ እነሆ፡-

·         ትምህርት ቤቱ፡- መስራታቸው በግልጽ የሚታይ  የቦርድ ተወካይ፤ የሃይማኖት መምህር እና የትምህረት ኮሚቴዎች አሉት

o   ለልጆች ትምህርት ቤት ብቻ የሚውል ብዙ ክፍሎች ያሉ አንድ ሙሉ ቤት ገዝተዋል

o   በደብሩ የታወቀ እና የተፈቀደ በፈንድ ሬዚንግ አድርገው በተለያየ ጊዜ 30 ሺ እና 40 ሺ ዶላር አሰባስበዋል

o   በደብሩ ሥር ያለ፤ የታወቀ የባንክ አካውንት አለው

o   የተጻፈ መተዳደሪያ ደንብ፤ የተሳለ አስተዳደራዊ መዋቅር፤ በቂ የማስተማርያ ቦታ አለው

o   በቋሚነት፤ ለልጆች ትምህርት ቤት የተቀጠረ የሃይማኖት መምህር (ካህን) አለው

o   እስከ 200 የሚደርሱ መደበኛ ተማሪዎች አሉ

o   የተጻፈ የቋንቋ ካሪኩለም/ሳምንታዊ ትምህርቶች/ አሉት

o   36 ቋሚ ነገር ግን በጎፈቃደኛ መምህራን አሉት

o   ወላጆች ተራ ወጥቶላቸው በየሳምንቱ መምህራንን ወይም ልጆቹን ይረዳሉ

o   የአካዳሚ ቱተር አገልግሎት ይሰጣል

o   ለውጤታማ ተማሪዎች ስኮላርሺፕ ይሰጣል

·         ተማሪዎች

o   ሦስት ምድብ አላቸው

§  ዕድሜ 5-7(ጀማሪ ደረጃ)     --ዕድሜ 8-12(መካከለኛ ደረጃ)  --ዕድሜ 13-18(የመጨረሻ ደረጃ)

o   የትምህርት ሰዓታቸው 7፡45-11፡00 ነው

o   በወር አንድ እሁድ ቅዳሴ እንዲያስቀድሱ ይደረጋል

o   የሚማሩት አማርኛ ቋንቋ፤ ሃይማኖት፤ እና ግብረ ዲቁና ነው

o   ዓመታዊ የምርቃት እና የጌት ቱጌዘር ዝግጅቶች አላቸው

·         መምህራን

o   በአንድ ክፍል 5 መምህራን ያስተምራሉ

o   አንድ መምህር አንድ ክብ ጠረጴዛ ይይዛል፤ በዕለቱ፤ በየጠረጴዛው በአማካይ ከ4-5 ተማሪዎች አይቻለሁ፡፡

o   በዕለቱ የሚያስተምሩት ትምህርት; በትምህረት ክፍሉ ተዘጋጅቶ ይሰጣቸዋል

o   የክፍል ፈተና ያርማሉ፤ ፈተና ይሰጣሉ፤

o   በቀጥታ ከወላጆች ጋር አይደራደሩም፡፡ የወላጆችን ኮሚቴ የወላጆችን  ጉዳይ ይይዝላቸዋል፡፡

·         የተማሪ ወላጆች

o   የደብሩ አባል መሆን አለባቸው

o   ክፍያ ይከፍላሉ (ለስናክ፤ ለአልባሳት፤ ለስቴሽነሪ የሚሆን)

§  በቤተሰብ፡- ለ1 ልጅ 10 ዶላር፤ ለ2 ልጅ 15 ዶላር፤ ለ3 ልጅ 20 ዶላር

o   የወላጆች አስተባባሪዎች አሉ

o   የወላጆች አለግልግሎት መመሪያ ማኑዋል ይሰጣቸዋል

o   ወላጆች በወር አንድ ጊዜ የሚያገለግሉበት መርሀግብር ይወጣላቸዋል

o   በስልክ፤ በኢሜይል፤ በአካል፤ በቤተክርስቲያን መድረክ ላይ ማሳሰቢያ እና ጥሪ ይደረግላቸዋል

o   በየሳምንቱ 15 ወላጆች (በየክፍሉ 5) ይመደባሉ

·         ኮሚቴዎች

o   ያነጋገርኳቸው አራት አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ናቸው

o   ያየኃቸው ግልጽ የሥራ ኃላፊነትያላቸው እና እርስ በእርሳቸው ደስ የሚል መግባባት ያላቸው ናቸው፡፡

o   ነባር እና የአገልግሎቶ ዓላማቸውን የሚያውቁ ስለሆኑ የአገልግሎቱን ውስጥና ውጪ፤ ድክመት እና ጥንካሬ ለይተው ያውቃሉ

o   በዲያስፖራ ወላጆች ውስጥ ያለ የልጅ አስተዳደግ ፓራዶክዶክስ እና የልጆች ማንነት ቀውስ ችግር በጥልቅ የተረዱ ስለሆኑ የትምህርት ቤቱን እንቅስቃሴ ይህንን ማኅራዊ ችግር በመፍታት ዙርያ እንዲቃኝ እየሞከሩ ነው፡፡

o   የሰጡኝ አክብሮት፤ ትምህርት እና ምክር የማይረሳ ነው፡፡

·         የስኬት መላዎች

o   ከወላጆች ጋር አንድ- ለአንድ ግብብነት መፍጠር

o   ደንቦችን ወላጆች እንዲያረቁ መጋበዝ፤ ከዚያ ማስፈጸም፤ ማስከበር፤ መሞከር

o   አገልግሎቱን በተገኘው አጋጣሚ እና መንገድ ሁሉ ማስተዋወቅ

o   ልጆች ቤተክርስቲያን ውስጥ ችሎታቸውን የሚያሳዩበት መድረክ (መነባንብ፤ ድራማ ወዘተ..) መፍጠር

o   ስኮላር ሺፕ፤ ሽልማት... መፍጠር
Measure of Success
  • Because of the kids school, the number of Church members increased by 30%
  • 100% of the kids that have passed through the school system are now in college
  • Those college kids (especially those who won the church's scholarship) serve back their church in their field of profession and preference.
  • Above all, the school is a proud source of well mannered, socially stable and academically competent citizens for the community.

The committee (ዶ/ር ሶሎሞን ገብሩ: ቢኒያም ገብረወልድ: ሐና ተስፋዬ: ቤተልሔም ዘውዴ: ) express their willingness to continue sharing their experience and resources as needed.

blessing

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡.......In The Name of The Father, The Son and The Holy Spirit. Amen.

Amen

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን::