የልጆቻችን
ትምህርት ቤት ከወላጆች ያገኛቸው እና የሚያገኛችው ብዙ ዓይነት አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች አሉ።
- የኮምፒውተር ወረቀቶች፤ እርሳሶች እና እስክሪቢቶዎች፤
- ኮምፒውተሮች፤ ፕሪንተሮች፤ የፕሪንተር ቀለሞች፤ የፕሮጀክተር ስክሪኖች፤
- አሻንጉሊቶች እና የምርቃት ዝግጅት ቁሳቁሶች
- ገንዘብ ወዘተ…በዓይን ከሚታዩት ነገሮች ዋና ዋናዎቹ ናችው።
በዓይን የማይታዩ፤ በገንዘብም የማይተመኑ ብዙ ዓይነት ስጦታዎችን ለምሳሌ:-
ጊዜ፤ ጉልበት፤ክህሎት፤ ፍቅር፤ ትዕግስት ወዘተን
… ለልጆቻችን የሚለግሱ ወላጆች እና ወጣቶችም አሉ።
ይህንንም
ማስታወሻ የጻፍኩት፤ የትምህርትቤታችን አስተዳደር እና አገልግሎት አድጎ እና ተደራጅቶ ለለጋሾችም ሆነ ለአገልጋዮች የምስጋና ደብዳቤ
ወይም ሰርቲፊኬት መስጠት እስኪጀምር ድረስ፤ ወይም የታክስ ክሬዲት ማሰጠት እስኪጀምር ድረስ፤ ወይም በተመደቡለት ካህን አማካኝነት
ለለጋሾች ሁሉ ቡራኬ እና አንድ አቡነ ዘበሰማያት ማስሰጠት እስኪጀምር ድረስ፤…. የጅምላ ምስጋና ለማቀረብ ነው። ዋናው ሰበቤ
ግን አቶ ሳልቫቶሬ ቡሽሜ ናቸው።
![]() |
አቶ ሳልቫቶሬ ሚካኤል ቡሽሜ |
አቶ ሳልቫቶሬ ይህንን
ልግስና ያደረጉት የልጆችን ትምህርት ቤት ጠጋ ብለው አይተው ምን ልርዳ? ከማለት በተጨማሪ ባለፈው እሁድ መምህራን ባደረጉት አስቸኳይ
ስብሰባ ላይ በአጋጣሚ ተገኝተው ከሰሙት የወንበር ችግር የተነሳ እንደሆን ገልጸውልናል።
![]() |
የተስፋ ወንበራችን |
እግዚአብሔር ቢፈቅድ
በቅርቡ የተለገሱንንም ሆነ የነበሩንን የልጆች ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች ሁሉ በአዲስ እና የተሻሉ የኮሌጅ መሳይ ወንበሮች ይተካሉ
ብዬ አምናለሁ። ያገለገሉትም ወንበርና ጠረጴዛዎችም፤ የልጆች ት/ት ክፍል እና የደብሩ አስተዳደር በመረጡት መንገድ ለምሳሌ ለሌላ
ደብር የልጆች መማርያ እንዲሆን በመለገስ፤ ወይም ሸጦ ገቢውን ለልጆች ት/ቤት ማጠናከሪያ ወይ ለቤተክርስቲያን መርጃ በማድረግ፤
ወይም በሌላ የተሻል አማራጭ ይወገዳሉ።
እቃዎች ሲያረጁ አርጅቶ የማይጣለው፤ አገልግሎቶች ሲረሱ በእግዜር ዘንድ ግን የማይረሳው የበጎ አድራጊዎች ቅንነት ነው። ለቤተክርስቲያን የተለገሱ ነገሮች ጥቅም ላይ ዋሉም አልዋሉም፤ የተደከሙ ድካሞች ፍሬ አፈሩም አላፈሩ፤ የአቅማቸውን የሰጡ እና የችሎታቸውን ያገለገሉ ሁሉ በጊዜው የእግዚብሔርን ስጦታ መቀበላቸው እንደማይቀር አምናለሁ።
እቃዎች ሲያረጁ አርጅቶ የማይጣለው፤ አገልግሎቶች ሲረሱ በእግዜር ዘንድ ግን የማይረሳው የበጎ አድራጊዎች ቅንነት ነው። ለቤተክርስቲያን የተለገሱ ነገሮች ጥቅም ላይ ዋሉም አልዋሉም፤ የተደከሙ ድካሞች ፍሬ አፈሩም አላፈሩ፤ የአቅማቸውን የሰጡ እና የችሎታቸውን ያገለገሉ ሁሉ በጊዜው የእግዚብሔርን ስጦታ መቀበላቸው እንደማይቀር አምናለሁ።
ስለዚህ…. በተለይ
- እርዱ ሳትባሉ «ምን ልርዳ?» ላላችሁ፤
- ለምኑኝ ሳትሉ የምትችሉትን ለሰጣችሁ፤
- «ቢያደርጉ ኖሮ» ከማለት ፋንታ «እኔ ልሞክረው » ብላችሁ ራሳችሁን የመፍትሔ አካል ላደረጋችሁ፤
- ልጅ ሳትወልዱ ወይ ተማሪ ልጅ ሳይኖራችሁ ከወላጆች በላይ ለልጆች ቋንቋ እና ሃይማኖት ለማስተማር ለተጋችሁ፤
- ከሳምንት ሳምንት አገር አቋርጣችሁ የልጆች ክፍልን ለረዳችሁ፤
- የዕለቱን ችግር ትታችሁ ወደ ፊት ልጆቻችን ማን ይሆናሉ? ማንንስ ይመስላሉ? ብላችሁ ለተጨነቃችሁ