Saturday, December 12, 2015

ወንበር ክፍልንም፤ አስተሳሰብንም ይለውጣል



በ ናዖድ ቤተሥላሴ
ለሁሉም ጊዜ አለው እንዲል መጽሐፉ፤ ቤተክርስቲያናችን እና ወላጆች ለልጆቻችን ትምህርት ቤት እንዲሟላ ከሚፈልጉት እና ከሚመኙት ነገሮች አንዱ የሆነው የመማርያ ወንበር ጉዳይ በአብዛኛው ተቃለለ።


በዚህ ዲሴምበር ውስጥ፤ ትምህርት ቤቱ ከቤተክርስቲያን አስተዳደር ባገኘው የአስቸኳይ ጉዳይ ብድር 120 (አንድ መቶ ሃያ) ወንበሮችን ለመግዛት ችሏል። ግዢው በአስቸኳይ ጊዜ ብድር የተከናወነው የወንበሮቹን ግዢ የት/ቤቱ አስተዳደርም ሆን የቤተክርስቲያኑ አስተዳደር በዚህ ዓመት እቅዳቸውም  በጀታቸው ይዘውት ስላልነበረ ነው። ግዥውን አስቸኳይ ያደረገውም ወንበሮቹ ዲሴምበር መጨረሻ በሚጠቃለል ታላቅ ቅናሽ ላይ በመቅረባቸው ነው።
አዲሶቹ ወንበሮች በአሁኑ ሰዓት ለመማሪያ ክፍሎቹም ሆን ለተማሪ ልጆቻችን ግርማ ሞገስን ሰጥተው፤ ለት/ቤቱ እና ለቤተክርስቲያኑም አስተዳደር ተስፋ ያለው የአገልግሎት ግብብነት እና ቅንነት መታሰቢያ ሃውልት ሆነው በየክፍሎቹ ተደርድረዋል።
እግር ጥሎት የመማርያ ክፍሎቹን የጎበኝ ወላጅም ሆን ካህን የሚያሳዩት መደሰት በራሱ ደስታ ይፈጥራል። ጎብኝዎች ታዲያ ከደስታቸው በኃላ ይሚናገሩት ቃላት ወንበሮቹ በሚያያቸው ላይ ሁሉ የአስተሳሰብ ለውጥ እያመጡ እንደሆነም ነው። ማስረጃ፦
1.      ሳይለመኑ ለወንበሮች ግዢ ሒሳብ ማወራረጃ የሚሆን የገንዝብ መዋጮ ይሰጣሉ ወይ ቃል ይገባሉ
2.      ካህናቶችም ለልጆቻችን ተጨማሪ አገልግሎት ሊሰጡ ቃል ይገባሉ (ለዚህም እነሆ በቅዳሴ ሰዓት ልጆቻችን በመማርያ ክፍሎች ሳሉ የማዕጠንት ቡራኬ ይደረግላቸው ጀምሯል)
3.      ነባር አገልጋዮች በግል እና በጋራ ሊያደርጓቸው የሚመኙትን ሃሳብ «ከእግዚአብሔር ጋር እንችላለን» በሚል መንፈስ ማሰማት ጀምረዋል
4.      አንዳንድ ግለሰቦች ጋር የነበረ «አስተዳደሮች እሺ አይሉም፤...» ወዘተ የሚል ስጋት እና ሰበብ ከአንደበታቸው ጠፍቶ ወድ «እንጠይቅ» እና «እናድርግ» ባይነት ሲሸጋገሩ አስተውያለሁ።
አዲሶቹ ወንበሮች ግን እንከን የላቸውም ማለት አይቻልም። ተማሪዎችም ሆነ አስተማሪዎች የተስማሙበት አንዱ እንከን የደብተር/ፎልደር ማስቀመጫ ኪስ ወይም ቦታ አለመኖር ነው። ለዚህ መፍትሔ የሚሆን መላዎችም በአስተዳደርም ሆን በግለሰቦች ዘንድ እየተብላሉ ናቸው። ወጪ ቆጣቢ መላ ካታያችሁ ጠቁሙን።
ሌላው እንከን ወንበሮቹ በምቾት ሲያገለግሉ የታየው እድሜያቸው ከ6 -13 ለሚደርሱ ተማሪዎች መሆኑ ነው። ለዚህም የተሻለ ጥናት እና መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ፤ ዕድሚያቸው ከ6 በታች ለሆኑ ተማሪዎቻችን በድሮዎቹ ወንበሮች እንዲገለገሉ ትተናችዋል (ከሃዘን ጋር)። የተሻለ መፍትሔ ካላችሁ ጠቁሙን።

ወንበሮቹን የገዛነው ከ እዚህ ነው ፤ ቅናሹ ሳያልፍ ሞክሩ።https://www.schooloutfitters.com/catalog/product_family_info/pfam_id/PFAM41827

ምስጋና ወ ወቀሳ ለየቀድሞዎቹ ጠርጴዛና ወንበሮች
 ይድረስ ለ ቀድሞ ወንበሮቻችን እና ጠረጴዛዎች።
በጊዜያችሁ ልጆቻችንን በትዕግስት ችላችሁ፤ ድንቅ አገልግሎት ሰለሰጣችሁን የእናንተንም ሆነ ወደ እኛ ያመጧችሁን በጎ አድራጊዎች ውለታ እግዚአብሔር ይቁጠርላችሁ። አሁንም ቢሆን ወይ ገንዝብ ወይ ልዩ አገልግሎት የመስጠት እድል ታገኙ ዘንድ ስቶር  በክብር አስቀምጠናችኋል።
ቢሆንም! ቢሆንም!  ድሮም አመጣጣችሁ ከየትምህርት ቤቱ አገልግሎታችሁን ጨርሳችሁ እኛ ላይ የተጣላችሁ ስለሆናችሁ ጎድታችሁንም ነበር።
  • 1ኛ   )   እኛን ወላጆችን፤ ለልጆቻቸው አዲስ ነገር መግዛት የማይችሉ የኔቢጤ አስመስላችሁን ነበር::
  • 2ተኛ)   በቤተክርስቲያን አስተዳደር ዘንድ የልጆች አገልግሎት «ትምህርት ቤት» በሚል ማዕረግ ታስቦ፤ በቂ በጀት እና ትኩረት እንዳላገኘ ላያችሁ ሁሉ እያሳበቃችሁ ስታሳቅቁን ነበር።
  • 3ተኛ)   ልጆቻንንም ያለ እድሚያቸው አስረጅታችሁ ተማሪ ሳይሆን ተጧሪ አስመስላችሁብንም ነበር ባይ ነኝ።
ይሄ ጉዳታችሁ የተገለጠልኝ መቼ እንደሆን ታውቃላችሁ! አዲሶቹ ወንበሮች ለጋ ልጆቻችንን በ «ወንበራዊ ፈገግታ» ፈገግ ብለው ሲያገልግሉ ባየሁ በመጀመርያው ቀን ነው።

አንባብያን ሆይ! «ወንበራዊ ፈገግታ» ምን ማለት እንደሆን ለመግለጥ ቃላት የለኝም። ለማወቅ ከፈለጋችሁ ግን መጀመርያ  በአዘቦት ቀን ኑ ና ባዶ ክፍል ተደብረው እዩዋቸው። ከዚያ ደግሞ እሁድ ኑና እዩዋቸው ወንበሮቹ ፈገግ  ብለው ታያላችሁ። ወንበሮቹ ሁሉ፤ ሁል ጊዜ ልጆች እንዲቀመጡባቸው የሚፈልጉ ይመስለኛል።

Friday, October 23, 2015

እግዚአብሔር የቅንነታችሁን ዋጋ ይክፈላችሁ

ከናኦድ ቤተሥላሴ


የልጆቻችን ትምህርት ቤት ከወላጆች ያገኛቸው እና የሚያገኛችው ብዙ ዓይነት አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች አሉ።
  • የኮምፒውተር ወረቀቶች፤ እርሳሶች እና እስክሪቢቶዎች፤
  • ኮምፒውተሮች፤ ፕሪንተሮች፤ የፕሪንተር ቀለሞች፤ የፕሮጀክተር ስክሪኖች፤
  • አሻንጉሊቶች እና የምርቃት ዝግጅት ቁሳቁሶች
  • ገንዘብ ወዘተ…በዓይን ከሚታዩት ነገሮች ዋና ዋናዎቹ ናችው።
በዓይን የማይታዩ፤ በገንዘብም የማይተመኑ ብዙ ዓይነት ስጦታዎችን ለምሳሌ:- ጊዜ፤ ጉልበት፤ክህሎት፤ ፍቅር፤ ትዕግስት ወዘተ… ለልጆቻችን የሚለግሱ ወላጆች እና ወጣቶችም አሉ።

ይህንንም ማስታወሻ የጻፍኩት፤ የትምህርትቤታችን አስተዳደር እና አገልግሎት አድጎ እና ተደራጅቶ ለለጋሾችም ሆነ ለአገልጋዮች የምስጋና ደብዳቤ ወይም ሰርቲፊኬት መስጠት እስኪጀምር ድረስ፤ ወይም የታክስ ክሬዲት ማሰጠት እስኪጀምር ድረስ፤ ወይም በተመደቡለት ካህን አማካኝነት ለለጋሾች ሁሉ ቡራኬ እና አንድ አቡነ ዘበሰማያት ማስሰጠት እስኪጀምር ድረስ፤…. የጅምላ ምስጋና ለማቀረብ ነው። ዋናው ሰበቤ ግን አቶ ሳልቫቶሬ ቡሽሜ ናቸው።

አቶ ሳልቫቶሬ ሚካኤል ቡሽሜ
ዛሬ 10/23/2015  ረፋዱ  ላይ ለልጆች ክፍል የሚጠቅሙ 30 የሚሆኑ ወንበሮች እና 26 ጠርጴዛዎችን በአቶ ሳልቫቶሬ ሚካኤል ቡሽሜ ተለግሰናል። እቃዎቹ ያገለገሉ ቢሆኑም የልጆቻችን ትምህርት ቤት የተሻሉ ወንበሮች እስኪገዛ ድረስ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ባየ ነኝ።
አቶ ሳልቫቶሬ ይህንን ልግስና ያደረጉት የልጆችን ትምህርት ቤት ጠጋ ብለው አይተው ምን ልርዳ? ከማለት በተጨማሪ ባለፈው እሁድ መምህራን ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ በአጋጣሚ ተገኝተው ከሰሙት የወንበር ችግር የተነሳ እንደሆን ገልጸውልናል።
የተስፋ ወንበራችን

እግዚአብሔር ቢፈቅድ በቅርቡ የተለገሱንንም ሆነ የነበሩንን የልጆች ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች ሁሉ በአዲስ እና የተሻሉ የኮሌጅ መሳይ ወንበሮች ይተካሉ ብዬ አምናለሁ። ያገለገሉትም ወንበርና ጠረጴዛዎችም፤ የልጆች ት/ት ክፍል እና የደብሩ አስተዳደር በመረጡት መንገድ ለምሳሌ ለሌላ ደብር የልጆች መማርያ እንዲሆን በመለገስ፤ ወይም ሸጦ ገቢውን ለልጆች ት/ቤት ማጠናከሪያ ወይ ለቤተክርስቲያን መርጃ በማድረግ፤ ወይም በሌላ የተሻል አማራጭ ይወገዳሉ። 

እቃዎች ሲያረጁ አርጅቶ የማይጣለው፤ አገልግሎቶች ሲረሱ በእግዜር ዘንድ ግን የማይረሳው የበጎ አድራጊዎች ቅንነት ነው። ለቤተክርስቲያን የተለገሱ ነገሮች ጥቅም ላይ ዋሉም አልዋሉም፤ የተደከሙ ድካሞች ፍሬ አፈሩም አላፈሩ፤ የአቅማቸውን የሰጡ እና የችሎታቸውን ያገለገሉ ሁሉ በጊዜው የእግዚብሔርን ስጦታ መቀበላቸው እንደማይቀር አምናለሁ።

ስለዚህ…. በተለይ 

  • እርዱ ሳትባሉ «ምን ልርዳ?» ላላችሁ፤ 
  • ለምኑኝ ሳትሉ የምትችሉትን ለሰጣችሁ፤ 
  • «ቢያደርጉ ኖሮ» ከማለት ፋንታ «እኔ ልሞክረው » ብላችሁ ራሳችሁን የመፍትሔ አካል ላደረጋችሁ፤ 
  • ልጅ ሳትወልዱ ወይ ተማሪ ልጅ ሳይኖራችሁ ከወላጆች በላይ ለልጆች ቋንቋ እና ሃይማኖት ለማስተማር ለተጋችሁ፤ 
  • ከሳምንት ሳምንት አገር አቋርጣችሁ የልጆች ክፍልን ለረዳችሁ፤ 
  • የዕለቱን ችግር ትታችሁ ወደ ፊት ልጆቻችን ማን ይሆናሉ? ማንንስ ይመስላሉ? ብላችሁ ለተነቃችሁ 
ቅን አገልጋዮች፤ ወላጆች፤ አስተማሪዎች እና ረዳቶች ሁሉ እግዚአብሔር የቅንነታችሁን ዋጋ ይክፈላችሁ።





Thursday, October 15, 2015

አሁን ያሉን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስኮች Current Volunteer Position at D.M. Kidus Mikael Cathedral Kids Dept

ለመምህራን እና ወላጆቸ በወር ወይ በሁለት ወር ወስጥ 1 ወይም 1/2 ካገኛችሁ፤ ለወር የሚበቃ ስራ ትሰራላችሁ። 
እግዚብሔር ጉልበታችሁን ይባርክ።

First= Pick a task and let me know what DAY and TIME you can volunteer.
Second= See me On Sunday to customize the task to fit your skill.
     PriorityUrgentHighMediumLow
All hands-on tasks do not require special skills.
All
 projects will be done by a team of two or three people with similar set of skills.


የሥራ
መደብ
& Priority

የሥራው  ዓይነት
የሥራ
ቀን/ የሚፈጀው
ሰዓት
የሥራው
ጠባይ
የሥራ
ቦታ/ሰዓት
A
Classroom (Urgent)
1-
Classroom
Teach, Assist Teachers, Assist Kids
Clean and Organize Rooms
እሁድ
30 ደቂቃ
Hands-on
ቤ/ክ
8-11


2-
Patrol Enforce Codes of
(Dressing, Time, Games, Wondering kids)
እሁድ
1 ሰዓት
Hands-on
ቤ/ክ
8-9


3-
Special Need Student Support
(Organize, Teach, Assist Teachers)
እሁድ
30 ደቂቃ
Hands-on
ቤ/ክ
8-11







B
Office (Urgent)
1-
Re-fill Classroom Kits
(Pencil Sharpening, Copying/ Binding
Typing/Editing, Filing/Labeling)
ሰኞ-ዓርብ
2 ቀን
በሳምንት
Hands-on
ቤ/ክ
11-5


2-
Inventory
(Record/Tag Recommend)
ሰኞ-ዓርብ
1/2 ቀን
በሳምንት
Hands-on
ቤ/ክ
11-5







C
IT
(High)
1-
Data
(Data Entry… Attendance, Forms…)
ሰኞ-ዓርብ
½ ቀን
በሳምንት
Hands-on
ቤ/ክ
11-5


2-
DB (MS Access)
(DB design)
-
1 ወር
Project
እቤት


3-
Web
(Write or Edit, Upload, Publish, Update)
-
1 ቀን
በሳምንት
Project
እቤት


4-
Computer svc
(Install, Configure, Maintain, Network)
-
1 ቀን
በወር
Project
ቤ/ከ-እቤት







D
R & D (Medium)
1-
Research
(Plan, Conduct, Summarize)
1 ቀን
በሳምንት
Project
ቤ/ከ-እቤት


2-
Training
(Staff & Parents)
(Announce, Register, Organize, Conduct)
እሁድ
1 ቀን
በሳምንት
Hands-on
ቤ/ከ-እቤት







E
Media (Medium)
1-
Print Media
(Teaching Aide (Design/Create, Write/Edit, Duplicate, Distribute))
2 ቀን
በሳምንት
Project
ቤ/ከ-እቤት

(Low)
2-
Digital Media
(Prepare Teaching Aides (Design/Create, Edit/Produce, Duplicate, Distribute))
1 ቀን
በሳምንት
Project
ቤ/ከ-እቤት







F
Extra
Curriculum (Low)
1-
Clubs
(Tutoring Kids, Field Day, Yaredawi Zema, Exhibition, Competition, Social Service)
½ ቀን በሳምንት
Project
Home


2-
Art & Craft
(Teaching Aide Design and production,
Spiritual Décor (posting church icons in classrooms))

Project
Home

blessing

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡.......In The Name of The Father, The Son and The Holy Spirit. Amen.

Amen

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር፤ አሜን::